Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
  • Address ሃያ ሁለት በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አለፍ ብሎ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ህንፃ 7ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111562305
  • Website
  • Deadline12 Jul 2024, 3:07 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Organizational

የመሬት ሊዝ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስታወቂያ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ከተማ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ፣ በየካ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በኮልፌ ቀራንዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በአዲስ ከተማ፣ ልደታ እና በጉለሌ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

  1.  ለአንድ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ሰነድ የማይመለስ ብር 2,300.00 (ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ብር) በቴሌ ብር በመክፈል የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ውን ሰነድ ከሐምሌ 01/2016 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት‍‍‍‍‍‌‌‌‍‍‌‌‌‍‌ ድረስ  
    • በ(2merkato.com link:- https://addisland.2merkato.com 
    • ወይም afrotender.com link: https://addisland.afrotender.com) መግዛት ይችላሉ።
  2. ማንኛውም በዚህ የመሬት ሊዝ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ለመሳተፍ የፈለገ ተጫራች በተራ ቁጥር 1 ላይ በተገለጸዉ ዌብ ሳይት የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ሰነድ ለመግዛት በመጀመሪያ በስሙ የቴሌ ብር አካውንት በመክፈት ከአካውንቱ ተቀናሽ በማድረግ ሰነዱን መግዛት ይጠበቅበታል።
  3. ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ቦታ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ አለባችሁ።
  4. አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም። በመሆኑም ከአንድ በላይ ቦታ ተጫርቶ ከተገኝ ተጫራቹ ከጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ውጪ ይሆናል።
  5. ተጫራቾቾ ሞልተው የሚያቀርቡት የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ላይ በቀረበው መስፈርት መሠረት መሆን ይኖርበታል።
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ የሚገኘውን ጠቅላላ ዋጋ 50% የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ ለየቦታ ኮዱ በጋዜጣው ላይ የተቀመጠውን መጠን ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 50% ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል። እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም። ከአዲስ አበባ ውጪ ከሚገኙ ባንኮች ሲፒኦ ስታሠሩ አዲስ አበባ ከሚገኙ ባንኮች በኔትወርክ የተያያዘ መሆን አለበት። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ችግር ቢፈጠር ጽ/ቤቱ አይጠየቅም።
  7.  ተጫራቾች የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ስትመልሱ፣
    • 7.1 ኦርጅናል ሲፒኦ (CPO)
    • 7.2 የመስሪያ ቤቱ ማህተም ያረፈበት የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ
    • 7.3 የተጫራቹ መታወቂያ ኮፒ
    • 7.4 ሰነድ ለመግዛት በቴሌ ብር የተከፈለበት ስሊፕ (ደረሰኝ)
    • 7.5 ኦርጅናል የአቅም ማሳያ ማስረጃ
    • 7.6 ተጫራቹ የሚጫረተው በተወካይ ከሆነ የተወካይ መታወቂያ እና የውክልና ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ አለበት። 
    • 7.7 የውጭ አገር ዜግነት ያለው በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ ማንኛውም ተጫራች ከሚኖርበት አገር በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ /ቆንስላ ጽ/ቤት/ የተሰጠውንና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ በውልና ማስረጃ የፀደቀ መታወቂያ የዋናውን ኮፒ ከመልስ ማቅረቢያው ጋር ማያያዝ አለበት።
    • 7.8 የንግድ ማህበራት ለሆኑት በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ፅ/ቤት የፀደቀ የማህበሩን መመስረቻ ፅሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ ሌሎች ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች ከሆኑ ሕጋዊነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ እና የታደሰ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው። 
    • 7.9 ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው የሚሳተፉት ባልና ሚስት በአንድ ሰነድ ከሆነ ህጋዊ የጋብቻ ማስረጃ ኮፒ እና በአንድ ወገን ስም የተሠራ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው። 
    • 7.10 በአንድ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ሰነድ ከአንድ ሰው በላይ ሆነው ለመወዳደር ከፈለጉ ከሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ፅ/ቤት የተረጋገጠ የተደራጁበትን ህጋዊ ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
    • 7.11 በአጠቃላይ ከላይ የተገለጹትን ማስረጃዎች በፖስታ በማሸግ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ቁጥር እና የቦታ መለያ ኮድ በፖስታዉ ላይ በመጻፍ ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ሕንጻ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  8. ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ይገለጻል። ተጫራቾች ቦታውን በአካል ለመመልከት ከፈለጉ በ05/11/16 ዓ.ም፣ 08/11/16 ዓ.ም እና በ10/11/16 ዓ.ም ጠዋት በ3፡00 እና ከሰዓት በ8 ሰዓት ለጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት ክ/ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚህ ሥራ በሚመደቡ አስጎብኝዎች አማካኝነት ቦታዎቹን መመልከት ይቻላል።
  9. ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ውን ያላሸነፉ (ተሸናፊ) ተጫራቾች ለጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስከበሪያ ያስያዙትን ሲፒኦ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው አሸናፊዎች በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከተገለፀበት ከ15 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አጫራቹ መ/ቤት ለባንክ በመላክ ወዳሠሩበት የባንክ ሂሳብ ተመላሽ ይደረጋል። በካሽ ያሠሩ ተጫራቾች የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስከበሪያ ዋስትናውን ለመረከብ በቅድሚያ የሲፒኦውን ጉርድ ኮፒ ማቅረብና ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርበው መውሰድ አለባቸው። ከላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ካልወሰዱ ለሚፈጠረው ችግር አጫራቹ መ/ቤት ተጠያቂ አይሆንም።
  10. መሥሪያ ቤቱ (ቢሮው) የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፡-
በስልክ ቁጥር +251111570595 መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
https://www.aalb.gov.et/
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

 
Save Tender