በድጋሚ የወጣ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የዶሮ ሥጋ፣ የእንቁላልና አሳ መሸጫ ሱቆች ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት አንድ ለአትክልትና ፍራፍሬ እና አንድ ለዶሮ ሥጋ፣ እንቁላልና አሳመሽጫ ብቻ የሚሆን የኮንተይነር ሱቅ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡-
- በመስኩ ወይም በተመሳሳይ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑ ግብርየከፈለ የማይመለስ ኮፒ በማያያዝ ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀዉ መሰረት ይሆናል፡፡
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮቁጥር 2 በመቅረብ መውሰድ ይችላል፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘውን የጨረታ ሠነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊትበተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታው ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በ4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውበተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በ8868/
0114163978/0114172877 ይጠይቁ ::
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
