የጨረታ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር ገንዘብ ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/90፤ 1147/11 እና 216/92 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረገዩ የተመለከቱትን ንብረቶች በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው/ የመያዣ ሰጪውስም |
የንብረትአድራሻ |
የንብረት ዝርዝር |
የቦታ ስፋት(በሄክታር) |
የጨረታ መነሻዋጋ (በብር) |
የጨረታ ሁኔታ |
የጨረታ ደረጃ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ኤም ኤን ኤስማኑፋክተሪንግ ኃ/ የተ/የግ/ማህበር |
በኦሮሚያብሔራዊክልላዊመንግስትበሸገርከተማአስተዳደርለገጣፎለገዳዲ ክ/ ከተማ |
የጨርቃጨርቅፋብሪካግንባታዎች! የኤሌክትሪክስራዎች፣ማሽነሪዎችናመሣሪያዎች፣ተሸከርካሪዎችግብዓቶችናየተጠናቀቁምርቶች |
106,638.95 ካሬሜትር |
2,306,801,435.60
|
ድርድር |
ሁለተኛ |
ነሃሴ 08 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00-6:00 ሰዓት |
|
2 |
ማጃንግ አግሮኢንዱስትሪ ኃ/የተ/ የግል ማህበር |
ጋምቤላ ህ/ብ/ክ/መ፤ማጃንግ ዞን፣መንገሺወረዳ፣ |
የመስኖ እርሻ እናግንባታዎች፣ የእርሻማሽነሪዎች፣ተሽከርካሪዎች፣ |
1000 ሄክታር |
241,180,405.31 |
ድርድር |
ልዩ ድርድር |
ነሃሴ 09 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00-6:00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ ፤
1. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የመያዣ ንብረት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታሰነድ በመግዛት ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በመጥቀስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድርቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን ለኤምኤን ኤስ ማኑፋክተሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ነሃሴ 08 ቀን 2016 ዓ.ምከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ፣ለማጃንግ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/ የተ/የግል ማህበር ነሃሴ 09 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓትድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
3. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል;፡
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ
በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ይካሄዳል፡፡
5. 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያንጨምሮ ገዢው ይከፍላል፡፡
6. አንዳንድ የድርጅቶቹ ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብትሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል፡፡
7. የድርጅቶቹ የስራ እንቅስቃሴ ያልተቋረጠ በመሆኑ አሸናፊው ከግዢው ዋጋ በተጨማሪ በመጓጓዝ ወይም በክምችትላይ ያሉ ግብዓቶች /ጥሬ ዕቃዎች/ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የተሰበሰቡ ምርቶችን በርክክብ ወቅት በሚደረስበትየትመና ዋጋ መሰረት በጥሬ ገንዘብ /በዱቤ/ ከፍሎ መውሰድ ይኖርበታል፣ እንዲሁም
8. ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው ከተቻለ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን አሸናፊው በባንኩብድር ፖሊሲና የአሰራር ስርዓት መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላና ፕሮጀክቱን የሚያስቀጥል ከሆነ ንብረቱንበከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል፡፡
9. የጨረታ አሸናፊው የድርጅቶቹን ቋሚ ሰራተኞች በሙሉ ከመብትና ጥቅማቸው ጋር መረከብ ይጠበቅበታል፡፡
10.በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው
11.በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅላይ በሚገኘው የኦንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክት እና አኳየርድ አሴት ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይምበስልክ ቁጥር 011--524-53-73/011-524-42-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ ንብረቱን መጐብኘት የሚፈልግከዳይሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፡፡
12.ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዩጵያ ልምት ባንክ
