የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለህሙማን አገልግሎት የሚውሉ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የኦፕራሲዮን ልብስ፣ የኦፕራሲዮን ጫማ፣ የውሃ፣ የኤሌክትሪክና የሁለገብ ጥገና እቃዎች፣ መድሃኒት ሪኤጀንትና ሳፕላይስ፣ የመኪና ጎማ ፣ የተለያዩ የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዉ ድርጅት ለመግዛት ይፈልጋል
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ፈ/ህ/አጠ/ስፔ/ሆ 02/2017
የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለህሙማን አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች፣ሎት 2 የኦፕራሲዮን ልብስ፣ ሎት 3 የኦፕራሲዮን ጫማ፣ ሎት 4 የውሃ፣ የኤሌክትሪክና የሁለገብ ጥገና እቃዎች፣ሎት 5 መድሃኒት ሪኤጀንትና ሳፕላይስ፣ ሎት 6 የመኪና ጎማ ፣ ሎት 7 የተለያዩ የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ በግልፅጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዉ ድርጅት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ጨረታ የሚወዳደሩ ድርጅቶች :-
1. በዘመኑ የታደሰና በዘርፋ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የግብር ከፋይነት መለያ /TN CARD /ሰርቴፊኬት ያላቸው፣
3. አጠቃላይ የአንድ አመቱ ድምር የገንዘቡ መጠን ከብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሽህ ብር እና በላይ ከሆነየተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብየሚችሉ፣
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተቁ 1- 3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች ስለጨረታዉ ዝርዝር መግለጫ እስፔስፊኬሽን/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋርተያይዟል፡፡
6. ተጫራቾች ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መወዳደር ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከሆስፒታሉ ዋና ገያዥ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ 16 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ስዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ማንኛውንም ግብር እና ታከስጨምሮ2/ሁለት ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/፤ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከዋስትና / ቢድ ቦንድ /ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ዋናውን ደረሰኝ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያዉ ቅፅ መሰረትየአንዱ ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በመሙላትና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥበጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆስፒታሉ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ፎቅ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 9 ለዚሁ ተብሎበተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16ቀናት 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሳጥኑም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4፡15 ይታሸጋል፡፡
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ግዥዎች ቢሮ በዚሁ ቀን ከቀኑበ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓትይከፈታል፡፡
11, ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. በጨረታው የሚሳተፋ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም
በስልክ ቁጥር 058 3205738/058 222 0916 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡- ፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባህር ዳር
የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
