የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ በ2017 በጀት ዓመት ለአካዳሚው ሰልጣኞች የሆቴል አገልግሎት የሚሰጡ በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ በ2017 በጀት ዓመት በጨረታ መለያ ቁጥር: አ/አ/አ/አካ/ግ/ጨ-0001/2017 ለአካዳሚው ሰልጣኞች የሆቴል አገልግሎት የሚሰጡ በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲሳተፉ ተጋብዟል፡-
- የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት
- የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (TIN)
- የአቅራቢነታችንን ሁኔታ የሚገልፅ ከመንግስት ግዥ ኤጄንሲ የተሰጠንን የምዝገባ ምስክር ወረቀት
- የተ.እ.ታ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
- ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ
- . የጨረታ ሂደቱ የመንግስትን የጨረታና የግዥ ሂደት የተከተለና በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ላይ በሚገኘው ዳብር ህንፃ ሦስተኛ ፎቅ የግዥ ዳሬክቶሬት ቢሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ በብር 200 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) የብር መጠን ያለው የጨረታ ማስከበሪያ “ለአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ” በሚል አድራሻ በባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ ባላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ወይም በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ካደራጃቸው መ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ “ለአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ” በሚል አድራሻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በሁለት(2) ኤንቬሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ተጫራቾች አስፈላጊ የሆኑ ህጋዊ ሰነዶችን፣ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)፣ ቴክኒካል ዶክመንቶችን በጨረታ ሰነዱ መሰረት እና ቴክኒካል የመወዳደሪያ ሰነዶችን የያዘ አንድ ሰነድ ኦርጅናል እንዲሁም ዋጋ የያዘውን ፋይናንሻል ሰነድ ኦሪጂናል ሰነድ በማዘጋጀት የሁለቱንም ኦርጅናል ሰነዶች አንድ፣ አንድ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከአካዳሚው በወሰዱት የጨረታ ሰነድ የተጠየቁትን ሞልተውና እያንዳንዱ ገጽ ላይ ማህተም በመምታት መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) የስራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡15 ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ አስራ አንደኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ በሚገኘው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አካዳሚው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስለ ጨረታው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ካስፈለገ ቀጥሎ ባለው የስልክ ቁጥር ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡-
0116-67-33-90/09 21 41 85 32
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ አዲስ አበባ
