የጋላፊ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሰራተኞች የመጠጥ ውሃ ግዥ ለመፈፀም ብቃትና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአምራች ድርጅቶች ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር CCGB/NCB/01/2017/24
ለጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሰራተኞች መስተንግዶ አገልግሎት የሚውል የታሸገ ውሃ ግዥጨረታ
1. የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ለሰራተኞች የመጠጥ ውሃ ግዥ ለመፈፀም ብቃትና ፍላጎት ያላቸውንተጫራቾች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአምራች ድርጅቶች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ጨረታውየሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት በመንግስት ግዥ አዋጅ በተገለጸውብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓት መሰረት ይሆናል፤ ባለ 2 ሊትር እና ባለ 1 ሊትር የታሸገ ውሃ ጨረታየሚከናወነው ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች እና ከአቅርቦቱ ጋር አግባብነት ያላቸው አምራች ድርጅቶች ሆኖ የታደሰህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልፅ ታክስ ክሊራንስ ከመንግስት ግዥናንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ ዌብሳይት ላይ የአቅራቢነት ዝርዝር (Supplier list) የአምራችነት ፈቃድ (CIO) ፕሪንት አድርገው ማምጣት የሚችሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬትማቅረብ አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው የጨረታ ሰነዱንአዲስ አበባ በሚገኘው ጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት መሿለኪያ ይርጋ ሀይሌ ፕላዛ ህንፃ 4ኛ ፎቅ በተገለፀውአድራሻ በአካል በመገኘት መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው አድራሻ ጨረታው ከወጣበትቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ የሚውል ሲሆን የጨረታ ሰነዱን እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውጭ ዘግይተው የቀረቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
- የመጫረቻ ሰነዶች በግልጽ የማይነበቡ፣ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች ዕቃውን ገቢ የሚያደርጉት በአፋር ክልል በኤሊደር ወረዳ በጋላፊ ቀበሌ በሚገኘው በጋላፊጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መሆኑ ይታወቅ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ/ ብርበCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የጨረታማስከበሪያውን በባንክ ዋስትና መልክ የሚያስይዙ ከሆነ የጨረታ ማስከበሪያው ዝቅተኛ የቆይታ ጊዜ (Minimum Bid Security Validity Date) 88 ቀናት መሆን አለበት። ከዚህ በታች ቢቀርብ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
5. የጨረታው ሰነድ የሚገኘበትና ሰነዱ የሚገባበት አድራሻ አዲስ አበባ መሿለኪያ ይርጋ ኃይሌ ፕላዛ ህንፃየሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 4ኛ ፎቅ ነው
6. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
አድራሻ፡-መሿለኪያ ይርጋ ሀይሌ ፕላዛ ህንፃ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ግዥና ፋይናንስ አስተዳደርዳይሬክቶሬት 4ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 0335 590 080
የጋላፊ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
