ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን በባይራ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የሞተር ሳይክል፣የጽህፈት መሳሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን በባይራ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት 2017 ዓ.ም በፑልለታቀፉ ሴ/ር መ/ቤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 01 የሞተር ሳይክል ፣
- ሎት 02 የጽህፈት መሳሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና
- ሎት 03 ኤሌክትሮኒክስ/
በመሆኑም በጨረታው ለመሣተፍ የምትችሉ ተጫራቾች፦
- ሕጋዊ በዘርፉ የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይነትመለያ ቁጥር ያላቸው እና 2% ለመንግስት ለመክፈል ፈቃደኛ የሆኑና ከሚመለከተው ክፍል የተሰጠ ታክስክሊራንስ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በፌዴራል ግዥና የመንግስት ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆንአለባቸው፤
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራሰዓት ለዶክመንቱ በየሎት የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳፋይናንስ ጽ/ቤት ከግዥና ንብረት አስ/ር የንግድ ፈቃዳቸውን ዋናውን (ኦሪጅናል/በመያዝ መግዛት ይችላሉ፣
- በሎት የሚፈለጉትን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ጥሬ ብር /ሲፒኦ/ 5,000/ አምስት ሺህብር/ ሲሆን በሎት 03 የተመዘገበው ለኤሌክትሮኒክስ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000/አስር ሺህ ብር/ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ ኦሪጅናሉንና ሁለት የኦሪጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በታሸገኤንቨሎፕ/ፖስታ/ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ በባ/ኮ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥንውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፤
- እስኪርብቶ፣ ቶነሮችን/ቀለም ናሙና ማቅረብ የሚችል፤
- ከጨረታው ሰነድ ውጪ ተሞልተው የሚወጣ ተቀባይነት የለውም፤
- የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቀጥሎበሚውለው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውበተገኙበት 4፡30 ሰዓት በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በግዥና ን/አ/ር ዳይሬክቶሬትቢሮ ይከፈታል፤
- በዋጋ ማቅረቢያ/በጨረታ ሰነድ ላይ የሚሞሉትን ዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ካልጨመሩ ቫትን እንዳለ ይወሰዳል፤
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ሰርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም፤
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ወረዳው ከወላይታ ዞን ርዕሰ ከተማ በስተምዕራብ በ9 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0956 445 021/0935 782 116 ደውለው ማነጋገር ይቻላል፤
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ
ዞን የባይራ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
