የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ለማስተላለፍ ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ 3 አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ሎት 1፡- ሱፐር ማርኬት፣ ሚኒ ማርኬት እና ጌም ዞን
- በዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና የ 2016 የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ወይም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ስም CPO (ጋራንትድ ቦንድ) በማሰራት ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከመጨረሻው ቀን በኋላ ለተጨማሪ 28 ቀናት ይሆናል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ-ዓርብ ከ2፡30-11፡00 ሰዓት ድረስ የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 803 ቀርበው ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን ማለትም የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለመገኘታቸው ምክንያት ጨረታውን ከመክፈት አያስቀርም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት (ማቅረብ) አይቻልም፡፡
- ቢሮው የገበያ ማዕከላቱ አይነት እና ብዛቱን በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ላይ በገለፅነው መሰረት መቀነስና መጨመር የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ማሸነፉ በቢሮው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ቢበዛ በ20 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከቢሮው ጋር ውል መግባት የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ በአግባቡ ማስገባት አለበት፡፡
- የፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ እንዲሁም የቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በሰም በታሸገ ፖስታ የድርጅቱ ማህተም እና በሚመለከተው ኃላፊ ተፈርሞ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ሀ. ቢሮው አዘጋጅቶ የሰጠውን የዋጋ መሙያ ሰነዱን ማህተም በማድረግ እሱኑ ሰነድ ኮፒ አድርጎ ዋናና ኮፒ በማለት በሁለት የተለያዩ ፖስታዎች አሽጎ ማስገባት አለበት፡፡
ለ. ቴክኒካል ሰነድ የሚያካትተው ንግድ ፍቃድ፣ ዋና ምዝገባ፣ የቫት ከፋይ ምስክር ወረቀት ኮፒ አድርጎ ማህተም በማድረግ እሱኑ በድጋሚ ኮፒ በማንሳት በተለያዩ በሁለት ፖስታዎች ዋና እና ኮፒ በማለት ማቅረብ (ማስገባት) አለበት፡፡ - ለተጫረተበት አገልግሎት (ለሱፐር ማርኬት፣ ሚኒ ማርኬት እና ጌም ዞን፣) የጠቅላላ ካሬ ዋጋ በወር ለመክፈል የሚጫረቱበትን/የሚወዳደርበትን ዋጋ ምንም ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በተሰጠው ኮድ ላይ በመሙላት ማስገባት አለበት፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 812 6179/ 011 170 3024/ በመደወል መረጃ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ደጃች ውቤ 1888 ህንፃ 8ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 803
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ
