በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ፅ/ቤት ለተለያዩ ትራክተሮች ጥገና አገልግሎት የሚውሉ መለዋወጫዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር LP/OT/005/OKSF1&3/2017
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ፅ/ቤት ለተለያዩ ትራክተሮች ጥገና አገልግሎት የሚውሉ መለዋወጫዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል ።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ /አዲስ የንግድ ፈቃድ ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ፣ በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን /መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ/ መረጃ ማቅረብ አለባቸው ።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚመለከተው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00 ፣ ከሰዓት ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ ።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የጥገና አገልግሎት ቀጥሎ የተመለከተውን የብር መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ።
ሎት-1 Spare part of YTO Tractor Model 1804 ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ብቻ
ሎት-2 Spare part of YTO Tractor Model 1004 ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ
ሎት-3 Spare part of URSUS Tractor Model 14014 ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ
ሎት-4 Spare part of YTO Tractor Model 1304 ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ። በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው 29/01/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 29/01/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል ። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል ።
- የጥገና አገልግሎቱ የሚከናወነው በደቡብ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ/መንግስት በማጂ ወረዳ እና በደቡብ ኦሞ ዞን በሰላማጎ ወረዳ የኦሞ ኩራዝ-3 ስኳር ፋብሪካ ።
- ጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው ።
- የጨረታው ማስረከቢያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ለ 90 ቀናት ነው ።
ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
ኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ
የግዥ ቡድን
አዲስ አበባ ካሳንችስ በተለምዶ መነኻሪያ ተብሎ ከሚጠራው ወደ አዋሬ
በሚወስደው መንገድ ከጨርጨር ስጋ ቤት ዝቅ ብሎ የፋብሪካው ማስተባበሪያ ቢሮ
የስልክ ቁጥር (አድራሻ) +251-913544731/+251910120628/+251930754814
አዲስ አበባ
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩብ የኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ፅ/ቤት
