በአዲስ ከተማ ጤና ጣቢያ የ2017 በጀት አመት መድሃኒት እና የህክምና እቃዎች እና LlS information ማሽን ሰርቪስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-002
በአዲስ ከተማ ጤና ጣቢያ የ2017 በጀት አመት በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ባወጣው ግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች የተዘጋጀ ግዥ
- lot 1 መድሃኒት እና የህክምና እቃዎች እና
- lot 2 LlS information ማሽን ሰርቪስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በመስኩ የተሰማራችሁ አቅራቢዎች፡-
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤
- የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር፣
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ሰርተፍኬት፤
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ lot 1 መድሃኒት እና የህክምና እቃዎች 2% (10,000)፤ lot 2 LlS information ማሽን ሰርቪስ /2,000/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር ጉዳዮች እና የተጫራቾችን መመሪያ የያዘ ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው የሚዘጋው በ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ታሽጎ 3፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ውል በተፈራረሙበት በ15 ቀን ውስጥ እቃውን ያቀርባል፡፡
- አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት በአካል በመቅረብ ስራውን ማከናወን አለበት፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው እና በእያንዳንዱ ላይ ገጽ ላይ ማህተብ እና ፊርማ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብም ሆነ ድርጅት ውል በሚይዝበት ወቅት ያሸነፈበትን የሽያጭ ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ማስያዝይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ 15% VAT ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጠቀስ ይኖርበታል፡፡ ካልተጠቀሰ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- ኦሪጅናል እና ኮፒውን ሰነድ ለየብቻ ተደርጎ በማያያዝ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የድርጅቱ ማህተብ ኦሪጅናሉ ላይ መደረግ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች መደበኛ የጨረታ ሰነዱን የሚሞሉ ክፍሎችን በአግባቡ ሞልቶ ተመላሽ ያላደረገ አቅራቢ ቅድመ ምርመራ ጨረታ ላይ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- የጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ልዩ አስተያየት የሚደረገው በሚያመርቱት ምርት ብቻ ሆኖ ከተደራጁበት ተቋም በሚያቀርቡት ደብዳቤ ይሆናል።
ተጨማሪ መረጃ፡- የጨረታ ሰነዱ የሚገኝበት ቦታ አ/ከ/ክ/ከ/ጤና ጣቢያ መሳለሚያ እህል በረንዳ ከእሳት አደጋ በስተጀርባ በሚገኘው የፋ/ግ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-2-75-62-04 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአዲስ ከተማ ጤና ጣቢያ
