Tender Detail

Tender Details

  • Company አምባሰል ንግድ ሥራዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (Ambasel Commercial Works P.L.C)
  • Address አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ከሚገኘው አምባስል ህንጻ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 503 ወይም አዲስ አበባ አምባሳደር ሲኒማ ያለበት ህንፃ አምባሰል ማእከላዊ ቅርንጫፍ ቢሮ 3ኛ ፎቅ የክልል ቅርንጫፍ መ/ቤቶች ( ባህር ዳር፣ ደሴ፣ ጎንደር) ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114701746
  • Websitehttps://www.ambaseltrading.com/
  • Deadline26 Oct 2024, 2:15 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Others

አምባሰል የንግድ ስራዎች ኃ/የተ/ግ/ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 05 በሚገኘው የኩባንያው መጋዘን ከውጭ አስገብቷቸው በተለያዩ ምክንያቶች በመደበኛ ሽያጭ ከክምችት ያላስወጣቸውን/ ያላስወገዳቸውን/ የተለያዩ አዳዲስ የኤሌክትሪክ ጀነሬተሮችና የውሃ ፓምፕ መለዋወጫዎች፣ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አዳዲስ ኖርማል ክላስ ሳይክሎችና መለዋወጫዎቻቸው፣ የቮልቮና የሌሎች መኪና መለዋወጫዎች፣ የሪል ማሽን (የመስኖ) መለዋወጫዎችና ድሪፕ ኢሪጌሽን (የጠብታ) ፓይፖች፣ የመርጫ መሳሪያ መለዋወጫዎች፣ የወኪንግ ትራክተር ተቀፅላዎችና መለዋወጫዎቻቸው፣የፓልምና የየሱፍ ዘይቶች ከነመያዣ ጀሪካኖቻቸው፤ እንዲሁም ሌሎች ንብረቶች ማለትም አገልግሎት የሰጡ ላፕ ቶፕና ዴስክ ቶፕ ኮምፒተሮችና ሌሎች የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ያገለገሉ ወንበርና ጠረጴዛዎች፣ የአልሙኒየምና የብረታ ብረት ቁርጥራጮች፣ ያገለገሉ የመኪና ጎማዎችና የመኪና ባትሪዎች፣ ግልባጭ ፒፒ ባጎችና ወዘተ… በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስታወቂያ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎

አምባሰል የንግድ ስራዎች ኃ/የተ/ግ/ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 05 በሚገኘው የኩባንያው መጋዘን ከውጭ አስገብቷቸው በተለያዩ ምክንያቶች በመደበኛ ሽያጭ ከክምችት ያላስወጣቸውን/ ያላስወገዳቸውን/

  • የተለያዩ አዳዲስ የኤሌክትሪክ ጀነሬተሮችና የውሃ ፓምፕ መለዋወጫዎች፣
  • በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አዳዲስ ኖርማል ክላስ ሳይክሎችና መለዋወጫዎቻቸው፣
  • የቮልቮና የሌሎች መኪና መለዋወጫዎች፣
  • የሪል ማሽን (የመስኖ) መለዋወጫዎችና ድሪፕ ኢሪጌሽን (የጠብታ) ፓይፖች፣
  • የመርጫ መሳሪያ መለዋወጫዎች፣ የወኪንግ ትራክተር ተቀፅላዎችና መለዋወጫዎቻቸው፣
  • የፓልምና የየሱፍ ዘይቶች ከነመያዣ ጀሪካኖቻቸው፤ 
  • እንዲሁም ሌሎች ንብረቶች ማለትም አገልግሎት የሰጡ ላፕ ቶፕና ዴስክ ቶፕ ኮምፒተሮችና ሌሎች የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
  • ያገለገሉ ወንበርና ጠረጴዛዎች፣
  • የአልሙኒየምና የብረታ ብረት ቁርጥራጮች፣
  • ያገለገሉ የመኪና ጎማዎችና የመኪና ባትሪዎች፣
  • ግልባጭ ፒፒ ባጎችና ወዘተ… በግልጽ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን፡፡

1. በዚህ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ለመሳተፍ የሚፈልግ ዕድሜው 18 አመት እና ከዚህ በላይ የሆነው ማንኛውም ተጫራች መሳተፍ ይችላል፡፡

2. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን በሎት ለተደራጁት ሸቀጦች /ንብረቶች/ ለተጫረቱት ሎትና ላቀረቡት ጠቅላላ የመግዣ ዋጋ 2% የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስከበሪያ (Bid        Bond) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ዋጋ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

3. ተጨራቾች የእያንዳንዱን ሎቶች የሸቀጥ / የንብረት/ ይዘትና ሁኔታ አዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 05 በሚገኘው አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር መጋዘን በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች በሎት ተለይቶ ወይም ተደራጅቶ በተቀመጠው መሰረት በሁሉም ሎቶች ላይ ወይም በከፊል መጫረት የሚችሉ ሲሆን የሎቶችን ዝርዝር የሚገልፀውን የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ሠነድ አምባሰል ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 503 ድረስ በመምጣት በማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ/ ብቻ ከፍለው በመውሰድ ሠነዱን ሞልተው በታሸገ ኢንቨሎኘ በማሸግ ከታች በተገለፁት  አድራሻዎች ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከታወጀበት እለት ከኦክቶበር 06, 2024  (መስከረም 26/ 2017 ዓ.ም) ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው በ21ኛው ቀን ማለትም በኦክቶበር 26, 2024 (ጥቅምት 16, 2017 ዓ.ም) ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት‍‍‍‍‍‌‌‌‍‍‌‌‌‍‌ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ሣጥኑ ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በሻጭ አድራሻ  አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 በተለምዶ ወሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ቦታ ኢትዮ ቻይና ወዳጅነት መንገድ አምባሰል ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 ላይ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ መከፈት ስነ- ስርዓቱን መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ መክፈት ስነ-ስርዓቱ የተጫራቾች ያለመገኘት ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ውን ዋጋ አያሳጣውም፡፡

6. የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ አሸናፊው አሸናፊነቱ በጽሑፍ እንደተገለጸለት /እንደታወቀ/ ባሸነፉበት የሎት አይነት የመግዣ ዋጋ መጠን መሰረት ለአምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 1000275128124 በማስገባት በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ማንሳት ይኖርበታል፡፡

7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ውን በከፊልም ሆን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡፡

ማሳሰቢያ ፡- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0114-70-17-46 /0114-66-61-45/ 09 35 403 334/ 09 13 009 194/

አምባሰል የንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር

Save Tender