Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ
  • Address ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት በኢግሥኮ-የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ 2ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116662390
  • Website
  • Deadline12 Jun 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-06-12 14:30:00
  • Categories Agriculture And Farming , Printing And Publishing , Others

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ በአዳማ ቅርንጫፍ የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


የተያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ- //////ግጨ/04/2018

 

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ በአዳማ ቅርንጫፍ የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

1.     በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስርነት ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስርነት ወረቀት (ሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡

2.     ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% ያላነሰ በባንክ የተመሰከረ CPO በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፓሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ ስም ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ 30 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡

3.     ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡የዕጣን ምርቶች ሽያጭ ተጫራቹ በሚሰጠው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይጨመራል፡፡

4.     ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በመፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከመጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው ፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ሀሙስ፣ ከሰዓት በፊት 200-600 ከሰዓት በኋላ 700-1030 እንዲሁም ዓርብ፤ ከሰዓት በፊት 200-530 ከሰዓት በኋላ 730- 10:30 በዘርፍ /ቤት ቃሊቲ ጉምሩ ፊት ለፊት በኢግሥኮ-የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልገሎት ዘርፍ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 አንዲሁም በአዳማ ከተማ መብራት ኃይል ንግድ ቤት ጎን አዳማ ቅርንጫፍ /ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

5.     ጨረታው ሰኔ 05 ቀን 2018 . ከሰዓት 800 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ሰኔ 05 ቀን 2018 . ከሰዓት 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው /ቤት በግብርና ውጤቶች እና ሜካናይዜሽን አገልግሎት በዘርፉ 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110 በኮርፖሬሽኑ አዳማ //ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፡፡

6.     ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከቀረበው ዝርዝር ምርቶች ውስጥ በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይቻላል፡፡

7.     ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፤

8.     ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግ ዘርፍ

አዲስ አበባ 011470-84-75/0116-66-23-90

አዳማ 022111-21-22/0221-11-31-56

 

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን-የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ

Save Tender