Tender Detail

Tender Details

  • Company የረጲ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
  • Address , Phone: 011-369-40-40
  • Website
  • Deadline13 Sep 2026, 9:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 300.00/ሶስት መቶ/ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • opening dateበ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Categories Education And Training , Office Supplies And Services , Printing And Publishing

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 11 አስተዳደር የረጲ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 የበጀት ዓመት የተለያዩ የትምህርት ግብአቶችን እንዲሁም የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 11 አስተዳደር የረጲ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 የበጀት ዓመት የተለያዩ የትምህርት ግብአቶችን እንዲሁም የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን ማለትም፤  ሎት 1 አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ ሎት2 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት3 መፅሃፍና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፤ ሎት 4 እድሳትና ጥገና ዕቃዎች፤ ሎት 5 የደንብ ልብስ፣ ሎት 6 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 7 የማሽነሪ ቋሚ እቃ፣ ሎት8 ህንፃ ቁሳቁስ ፣ ሎት 9 የጥገና ስራዎች፣ ሎት 10 የላብራቶሪ እቃዎች፣ ሎት11 ልዩ ልዩ እቃዎች፣ ሎት 12 የህትመት ስራዎች፤  ሎት13  የመምህራን መዝናኛ ካፌ የምግብ አቅርቦት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።  ስለዚህ

1.      በመንግስት እቃ አቅራቢነት ተመዝግቦ የምስክር ወረቀት ያለው።

2.    ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

3.    ተጫራቾች ለተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

4.    ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ/ብር ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከአል-ሰላም ዳቦ ቤት ወይም ታክሲ ተራ 100ሜ አለፍ ብሎ በረጲ የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር-03 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ ቀናት በተጠቀሰው የቢሮ ቁጥር በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

5.    የጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ናሙና ወይም ሰነድ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

6.    አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።

7.    ገዢው በአካል የሚገዛውን እቃ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።

8.    ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ እና መደበኛ የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛ ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9.    ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።

10.   ጨረታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ ብር ሎት1፣ ሎት2፣ ሎት3፣ ሎት4፣ ሎት5፣ ሎት6፣ ሎት7፣ሎት8 ብር 60,000 /ስልሳ ሺ ብር/ ለእያንዳንዱ ሎት እንዲሁም ሎት-09፣ ሎት10፣ ሎት11፣ ሎት12፣ ሎት 13 ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺ/ ብር ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ የተረጋገጠ/ሲፒኦ/ ተጫራቾች ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊዉ ድርጅት ከታወቀ በኋላ ለተሸናፊዎች ያስያዙትን ሲፒኦ /C.PO/ ወዲያዉኑ ይመለሳል።

11.    የእቃው ማስረከቢያ ቦታ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ በረጲ የመጀ/ደ/ት/ቤት ንብረት ክፍል ይሆናል።

12.   በሚቀርበው በመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ የድርጅቱ ሃላፊ ስምና ፊርማ፣ የድርጅቱ አድራሻ፣ የድርጅቱ ማህተም እና የስልክ ቁጥር መኖር አለበት።

13.   ት/ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 8 ወር ድረስ ውሉን ቢያድስም ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

14.   አሸናፊዉ ተጫራች ማሸነፋ ከተገለፀበት ከ7ኛዉ ቀን ቀጥሎ ዉል መፈፀምና 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO ማስያዝ አለበት።

15.   የእቃ ማጓጓዣ አሸናፊው ድርጅት የሚሸፍን ይሆናል።

16.   ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡- በኮ/ቀ/ክ/ከ ወረዳ 11 የረጲ የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ሲሆን

 ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-011-369-40-40 /011-369-39-94

 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ -11 አስተዳደር ት/ጽ/ቤት የረጲ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

 

 የረጲ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

Save Tender