Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር የሁሩሙ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙት ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል፡ የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ እና የተለያዩ የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ ጥሪ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር የሁሩሙ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙት ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል፡ የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ እና የተለያዩ የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ።

ተቁ ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ቀን ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት የዕቃው ዓይነት የጨረታው ቁጥር የጨረታው መክፈቻ ቀን ሰዓት
1 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ጋዜጣው አየር ላይ በዋለበት 16 ቀን የጽህፈት መሣሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች 1  
2     የፈርኒቸር ዕቃዎች 2  
3     የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 3  
4     የደንብ ልብስ ዕቃዎች 4  
5     የመኪና ጎማዎች 5  
6     የግንባታ ዕቃዎች 6  
7       7  
  • በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችል እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ።
  • በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገበ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  • ለጨረታ ማስከበሪያ 20000 (ሀያ ሺህ) ብር በሲፒኦ (CPO) ማስያዝ የሚችልና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ለጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ የሚችል።
  • ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈ 3% WITHHOLDING ታክስ መክፈል የሚችል።
  • ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ለበጀት ዓመቱ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ የሆነና ዕቃዎቹን በራሱ ሙሉ ወጪ በታዘዘ ጊዜ ውስጥ እስከ ጽ/ቤቱ ለማቅረብና ቆጥሮ ለማስረከብ ፈቃደኛ የሆነ።
  • ተጫራቹ የዕቃውን ሞዴል ባልተገለጸበት ቦታ በጨረታው ዝርዝር ላይ መግለጽ አለበት።
  • ተጫራቾች የተፈለገውን ዕቃ ጥራትና ብዛት አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  • ተጫራቹ ለሚያቀርባቸው የደንብ ልብሶች እና የጽህፈት መሣሪያዎች ሳምፕል (ናሙና) ማቅረብ ይኖርበታል።
  • ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር የሁሩሙ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በመግዛት የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ ሰነድ በመውሰድ የአንዱን ዋጋ በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
  • ተጫራቾች በሌላ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው።
  • የሚወዳደሩበት ሰነድ ሰርዝ ድልዝ የሌለው እና የሚነበብ መሆን አለበት።
  • ተወዳዳሪዎች ዋጋን የሚገልጽ ሰነድ እና ፍቃድ የተለያዩ ተፈላጊ ሰነዶችን ኦሪጅናል እና ኮፒ በታሸገ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910989873 እና 0941483877

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በኢሉአባቦር ዞን የሁሩሙ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት

Save Tender