በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ለብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2019 የተለያዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ለብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2019 የሰራ ዘመን የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ህትመት፣ አላቂ የህክምና እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ ሌሎች አላቂ እቃዎች፣ ለመስተንግዶ(ሻይ ከበብ)፣ ለህንፃ ቁሳቁስ እቃዎች መግዣ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳትና ጥገና፣ ለፕላን ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ መግዣ፣ ልዩ ልዩ ክፍያዎች እና ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች መግዣ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | የእቃው አይነት | የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(cpo) |
| ሎት 1 | የደንብ ልብሶች | 18,000.00 (አስራ ስምንት ሺህ ብር) |
| ሎት 2 | አላቂ የቢሮ እቃዎች | 19,000.00 (አስራ ዘጠኝ ሺህ ብር) |
| ሎት 3 | ህትመት | 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) |
| ሎት 4 | አላቂ የህክምና እቃዎች | 16,000.00 (አስራ ስድስት ሺህ ብር) |
| ሎት 5 | አላቂ የትምህርት እቃዎች | 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) |
| ሎት 6 | ሌሎች አላቂ እቃዎች | 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር) |
| ሎት 7 | ለመስተንግዶ(ሻይ ከበብ) | 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) |
| ሎት 8 | ለህንፃ ቁሳቁስ እቃዎች መግዣ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳትና ጥገና | 21,000.00 (ሃያ አንድ ሺህ ብር) |
| ሎት 9 | ለፕላን ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ መግዣ | 23,000.00 (ሃያ ሶስት ሺህ ብር) |
| ሎት 10 | ልዩ ልዩ ክፍያዎች | 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር) |
| ሎት 11 | ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች መግዣ | 22,000.00 (ሃያ ሁለት ሺህ ብር) |
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር (በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡበትን የአቅራቢነት ማስረጃ)፣
- በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርቡ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ለእያንዳንዱ የእቃ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ የተገለጹትን የገንዘብ መጠን ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጋራንቲ ወይም በባንክ በተረጋገጠ cpo ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ የድጋፍ ደብዳቤ(cpo) ለሚያቀርቡ ተጫራቾች ደብዳቤው ባደራጃቸው ዋና ፅ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ11ኛው ቀን በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ጠዋት 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ግዥ ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል።
- በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በት/ቤቱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር12 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰንጠረዡ በተጠቀሰው የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰአት በፊት በግዥ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ከላይ በተገለጸው የመከፈቻ ቀንና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ግዥ ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሆነው አካል ያሸነፈበትን እቃዎች መስሪያ ቤቱ ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርበታል።
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን ሁሉንም የመስተንግዶ (ሻይ ከበብ) አገልግሎቶች ባስቀመጠው የዋጋ ዝርዝር መሰረት እንዲሁም ጥራቱን እና ንፅህናውን የጠበቀ አገልግሎቶችን በተጠቀሰው ቦታ ቀን እና ሰዓት የማቅረብ ግዴታ ይኖርበታል፣ እንዲሁም የአቅራቢው ደረሰኝ ቲኦቲ መሆን ይኖርበታል፡፡
አድራሻ፡- ኮ/ቀ/ከ/ከ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት ከአለርት ሆስፒታል ጀርባ ።
ለበለጠ መረጃ:- 0113-21-13-94/0113-69-95-35
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ለብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት
