Tender Detail

Tender Details


በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በስሩ ላሉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በስሩ ላሉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1.      ሎት 1 አላቂ የቢሮ ዕቃዎችና የፅህፈት መሣሪያዎች /ሲፒኦ ማስያዣ ለቀረቡት ዕቃዎች ዋጋ 2%/

2.    ሎት 2 የጽዳት እቃዎች /ሲፒኦ ማስያዣ ለቀረቡት ዕቃዎች ዋጋ /2%/

3.    ሎት 3 የደንብ ልብስ /ሲፒኦ ማስያዣ ለቀረቡት ዕቃዎች ዋጋ /2%/

4.    ሎት 4 የህትመት ስራዎች 10,000/አስር ሺህ ብር/

5.    ሎት 5 የመስተንግዶ አገልግሎት 10,000 /አስር ሺህ ብር/

6.    ሎት 6 የትራንስፖርት እና የጭነት አገልግሎት 10,000 /አስር ሺህ ብር/

7.    ሎት 7 የጉልበት ስራ አገልግሎት 10,000 /አስር ሺህ ብር/

8.    ሎት 8 የሞንታርቦ ኪራይ እና የአዳራሽ ዲኮር አገልግሎት ለእያንዳንዱ አገልግሎት 10,000 / አስር ሺህ ብር/ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ሲፒኦ ማሰራት ይጠበቅባቸዋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

1.      የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የገበሩ፤

2.    የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

3.    በመንግስት ግዥ የአቅራቢነት ዝርዝር ላይ የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ወረቀት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፤

4.    ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 ለተቀመጡት ዝርዝሮች ያስገቡትን የዕቃ ዋጋ 2% እና ሌሎች ለተዘረዘሩ አገልግሎቶች በየሎቱ በተገለጸው የብር መጠን መሰረት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ሲፒኦ ማሰራት ይጠበቅባቸዋል።

5.    ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 400/አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።

6.    በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ለሚሰሩ ከስራና ክህሎት ጽ/ቤት የትብብር ደብዳቤ በማምጣት በተፈቀደላቸው ዘርፍ ላይ ብቻ ያለ ክፍያ የጨረታ ሰነድ መውሰድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሳያሲዙ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ከሚያመርቱት ምርት ውጭ በሆነ ዕቃዎች ላይ እንደማንኛውም ነጋዴ የጨረታ ሰነድ መግዛትና ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

7.    ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይጠበቅበታል።

8.    ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ፣ስርዝ ድልዝ የሌለው ዋጋ መሙላትና ሙሉ የጨረታ ሰነዱን ከሚያስገቡት ዶክመንት ጋር በማያያዝ ተመላሽ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

9.    ናሙና በሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ጨረታው አየር ላይ እስከሚቆይበት ጊዜ ብቻ ናሙናውን ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

10.   ጨረታዉ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ የሚቆይ ሲሆን በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

11.    አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ማሳሰቢያ፡- ለናሙና ማስቀመጫ በቂ ቦታ ስለሌለን የጨረታው ሂደት እንደተጠናቀቀ በ1 ወር ውስጥ ያቀረባችሁትን ናሙና እንድትረከቡ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው የንብረት ብክነት እና ብልሽት ሃላፊነት የማንወስድ መሆኑን እንገልፃለን።

አድራሻ፡-ሕ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት ልዩ ቦታ

ተክለሃይማኖት በርበሬ በረንዳ

 

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender