የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የባህር ዛፍ ቆረጣ እና የማገዶ እንጨት ማዘጋጀት፣ የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ እና በተዘዋዋሪ ፈንድ የእንስሳት መድሀኒት ግዥ በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
- የባህር ዛፍ ቆረጣ እና የማገዶ እንጨት ማዘጋጀት ግዥ ጨረታ ሎት-01
- የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ግዥ ጨረታ ሎት-02
- በተዘዋዋሪ ፈንድ የእንስሳት መድሀኒት ግዥ ጨረታ ሎት-03
ከላይ ከሎት 01-03 የተጠቀሱት ግዥዎችን ለመፈፀም የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ለ2016/17ዓ/ም በዘርፉ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ ለ2016/17ዓ/ም የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በሀገር ውስጥ ገቢዎች የጨረታ ተሳታፊነት የድጋፍ ደብዳቤ ያላቸው የታደሠ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ካላቸው ተወዳዳሪዎች በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፤-
- ዝርዝር ጨረታውን የያዘ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/በመክፈል አሶሳ በቤ/ጉ/ ክ/መ/ ግብርና ቢሮ በግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የውል ስምምነት ሲፈርም ለውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ያሲይዛል፡፡
- በጨረታው ያልተመረጡ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበረያ የጨረታ አሸናፊ እንደታወቀ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሠነዱን በመግዛት እስከ 16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሆኖ ነገር ግን ቅዳሜ፧እሁድ እና የህዝብ በዓል ቀን ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘጋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አሶሳ በሚገኘው በቤ/ጉ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ በግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ይሆናል።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 057 775 2144 አሶሳ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፤
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ
