የአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ የተለያዩ ውፍረት ያላቸው ባህርዛፎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፣ አቤሜኢ/ሰቼማ/ግጨ/2017/01
የአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ የተለያዩ ውፍረት ያላቸው ባህርዛፎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የግብር መክፈያ ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥና በግብር ሰብሳቢ ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ቅጂ፣ አግባብ ያለው የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ቅጂውን፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና የግብር መክፈያ መለያ ሰርተፊኬት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በአቃቂ ቤዚክ ሜታል ኢንዱስትሪ ስም ሒሳብ ቁጥር 1000014630906 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ይዘው ኢንዱስትሪያችን በመቅረብ ከሽያጭ ክፍል ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) በCPO ወይም bank guarantee ወይም Cash ቢያንስ ለ88 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 1ኛ ወለል ሽያጭ ከፍል ቢሮ ቁጥር 34 ውስጥ ይከፈታል፣
- ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፣
- ኢንዱስትሪው ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ባለ አንድ ኤንቨሎፕ ሲሆን ፋይናንሻል በአንድ ኤንቨሎፕ አሽጐ ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት በክፍሉ በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
አድራሻ ፡- ከአ/አ ወደ ዱከም መሄጃ መንገድ ላይ ከሚገኘው ገላን ከተማ ሳይደርስ ሸገር ከተማ አቃቂ የፍተሻ ጣቢያ (ኬላ) አጠገብ ከASTCO FOOD COMPLEX በቀኝ በኩል ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 011 43 409 19/ 0114340918
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ
