Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት
  • Address ኮምቦልቻ ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 033 351 33 37
  • Website
  • Deadline17 Nov 2024, 5:30 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Machinery

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በ2017 በጀት አመት ከመደበኛ በጀት አመታዊ ማሽነሪዎች እና የተሽከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን /ቤት 2017 በጀት አመት ከመደበኛ በጀት አመታዊ ማሽነሪዎች እና የተሽከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በዘመኑና በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በአካባቢያችን /በኮምቦልቻ ከተማ/ ጋራዥ /ቅርንጫፍ ጋራዥ/ ስለመኖሩ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 40 ቀናት ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND) ብር የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በማስላት በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዢያ (CPO) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማቅረብ አለበት፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች /ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በሚጠይቀው የዋጋ አሞላል ብቻ መሙላት አለበት፡፡ በሚጠይቀው ዋጋ አሞላል ካልሞሉ የጨረታ ሰነዱ ውድቅ ይሆናል፡፡
  8. የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በሎት /በጥቅል/ ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም፡፡ ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ከጨረታው ውድቅ ይሆናሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ከግ/ፋይ//አስ//የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 24/02/2017 . እስከ 08/03/2017 . 1130 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ አንድ ቅጂ ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ መንገዶች ባለስልጣን /ቤት በግዥና/ፋይ//አስ//የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 09/03/2017 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  13. ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋይ/ አስ//የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 09/03/2017 . 400 ሰዓት ታሽጎ 430 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ፣ እሁድና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻልን፡፡
  14. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ለበለጠ መረጃ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን /ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልከ ቁጥር 033-3-51-33-37/ 033-5-51-05-04 መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  16. ማሳሰቢያ፡- የመስሪያ ቤቱ አድራሻ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ህንጻ አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 ላይ ነው፡፡

 

በአብክመ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር

 መንገዶች ባስስልጣን መ/ቤት

Save Tender