ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በስሩ ለሚገኘው ለቢሾፍቱ ዶሮ ልማት የሚውል መጠኑ 15,000 እስር ወይም 210,000 ኪ.ግ የሆነ የጤፍ ጭድ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ እና ግብዓቶችን በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ ከሚችሉ ልምድና ብቃት ያላቸውን አቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EL/LP-04/2024
ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በስሩ ለሚገኘው ለቢሾፍቱ ዶሮ ልማት የሚውል መጠኑ 15,000 እስር ወይም 210,000 ኪ.ግ የሆነ የጤፍ ጭድ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ እና ግብዓቶችን በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ ከሚችሉ ልምድና ብቃት ያላቸውን አቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
-
-
- ተጫራቾች አግባብነት ያለዉ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ወይም ተርን ኦቨር ታክስ (TOT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚመለስ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ለመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ጠቅላላ ካሸነፈው አቅርቦት መጠን ላይ 10% በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ በተዘረዘረው እና በተያያዘው የአቅርቦትና የጥራት መሥፈርት መሠረት ጨረታውን መጫረት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ላም በረት አካባቢ ከሚገኘው የድርጅቱ አቅርቦት መምሪያ በስራ ሰአት በመምጣት የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
- የጨረታው ሰነድ ሳጥን ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላምበረት በሚገኘው አዲሱ የኤልፎራ ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ በሚገኘው ኮሜርሻል ዘርፍ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይካሄዳል፡፡
- አቅርቦት መጠንን በተመለከተ እንደ ሁኔታው መጠኑ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
-
ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር +251116461076/0911625992/0/0911330099 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
