የእንፆኪያገ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤትግዥ/ንብ/አስ/ቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የእንፆኪያገ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤትግዥ/ንብ/አስ/ቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1 የጽ/መሣሪያዎች፣
- ሎት 2 የእንስሳት ህክምና ማቴሪያል እና ቁሳቁስ፣
- ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣
- ሎት 4 የውጭ ፈርኒቸር፣
- ሎት 5 ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ፣
- ሎት 6 የማሽነሪ ጥገና፣
- ሎት 7 የጽዳት እቃ፣
በየዘርፉ ንግድ ፈቃዳቸው በሚጋብዛቸው መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፤
- ተጫራቾች ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50 በመከፈል ከ29/3/2017 እስከ 14/04/2017 ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ግ/ፋ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ላይ እና ዋጋ መሙያው ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በግልጽ በማስቀመጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይቻላል።
- የጨረታ ሳጥኑ በ14/04/2017 በ4፡01 ሰዓት ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት በዚሁ ቀን በ14/4/2017 በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደ ተጫራቾቹ ምርጫ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በጥሬ ገንዘብ /CPO/ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች አሸናፊ ውል ከፈጸመ በኋላ የሚመለስ ሲሆን፤ ለአሸናፊው ድርጅት ውል ፈጽሞ 10 % የውል ማስከበሪያ እንዳስያዘ የጨረታ ማስከበሪያው ይመለስለታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸለት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መግባት ይጠበቅበታል፤ ያስያዘው 10% የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን እቃ ሙሉ አንፆ/ገ/ወ/ግዥ ንብ/አስ/ቡድን መጋዘን ካስረከበ ከ30 ቀናት በኋላ ይመለስለታል፡፡
- በሎት1፣ 2፣3፣4፣ 5፤ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- መ/ቤቱ የሚገዛውን እቃ ብዛት 20% የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው፡፡
- ተጨማሪ መረጃዎችንና የጨረታ ሰነድ በአንፆ/ገ/ወ/ግ/ፋ/ን/አስ/ቁጥር 01 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ውድድሩ የሚደረገው በእያንዳንዱ ሎት በጥቅል ድምር ዋጋ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 444 00 11 /033 444 04 25 ይጠይቁ።
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ የመክፈቻው ቀን በአል ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጠጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
በአብክመ በሰ/ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የአንፃኪያ ገምዛ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
