የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ተረፈ ምርቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
የተረፈ ምርት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ሽ/08/2017
የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ተረፈ ምርቶች ማለትም፡-
ሎት 1 - የፕላስቲከ ከረጢቶች
ሎት 2 - ስስ ፌስታሎች
ሎት 3 - የፕላስቲክ ፓሌት ጣውላ
ሎት 4 - የእንጨት ፓሌት ጣውላ
ሎት 5 - የካኪ ከረጢቶች
ሎት 6 - የፒፒአር ፓይፕ
ሎት 7 - የፍላት ሆዝ ፓይፕ
ሎት 8 - የዩፒቨሲ ፓይፕ ራቨር ሲሎችን እና
ሎት 9 - የGreen house sheet እና የcommon plastic sheet ተረፈ ምርት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ (መወዳደር) ይችላሉ፡፡
- ተረፈ ምርቶችን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት የንግድ ፈቃድ እና ሌሎች የሕጋዊነት ሠነዶችን ማቅረብ ሳይጠበቅበት በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም ከባንክ በፋብሪካው ስም በተዘጋጀ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከፋብሪካው ገንዘብ ያዥ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 መግዛት ወይም በኢ-ሜይል (e-mail) አድራሻ amharapipefactory@gmail.com ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ፣ የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችን ማስረጃዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 206 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 206 ከቀኑ 8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- 16ኛው ቀን ሕዝባዊ በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚሸጡት ተረፈ ምርቶችን በአካል በፋብሪካው አድራሻ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡00-5፡00 ማየት ይችላሉ፡፡
- ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0935-98-37-29/09-18-08-18-26 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ማህበር
