Tender Detail

Tender Details


ዳዬ በንሳ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር እና እህት ድርጅቶች ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ለቡና መፈልፈያ ኢንዱስትሪ ግንባታ የሚያስፈልጉ የአካባቢ ዕቃዎችን እና የፋብሪካ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


ዕቃ ለመግዛት የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ድርጅታችን ዳዬ በንሳ ቢዝነስ /የተ/የግ/ ማህበር እና እህት ድርጅቶች ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ለቡና መፈልፈያ ኢንዱስትሪ ግንባታ የሚያስፈልጉ የአካባቢ ዕቃዎችን እና የፋብሪካ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ እነርሱም

1.     ሎት፡- 1 የአባቢ ዕቃዎች /Local Materials -

1.1 ቀርከ 1.2 ለጉልቻ የሚሆን ባህርዛፍ 1.3 ፋና፡ 1.4 ቅርጮ 1.5 ማገር 1.6 ጠርብ፡ 1.7.ሞራሌ፡

1.8 ለጉልቻ የሚሆን ጠርብ፡

2.     ሎት፡-2 የፋብሪካ እቃዎች:-

2.1 ንቶ 2.2 ስማር 2.3 የቤት ዳን ቆርቆሮ 2.4 የመብራት ሽቦ 2.5 የመኪና ሸራ (ፕላስቲክ) 2.6 የእጅ ባትሪ (ባለ ቻርጅ) 2.7 አምፖል -60A 2.8 የአምፖል አቃፊ 2.9 የወንፊት ሽቦ 2.10 የአጥር ሽቦ 2.11 ጌት ቫልቭ ሲሆኑ ስለ ዕቃዎቹ - ሙሉ ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነድ ላይ ያገኛሉ

በዚህም መሠረት ተጫራቾች ማሟላት ያለባችው መረጃዎች:-

1.     ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት የተመዘገቡና የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ጊዜው ያላለፈበትን ከገቢዎች ሚኒስቴር የተሰጠ ክሊራንስ ወይም የድጋፍ ደብዳቤ እና በግዥ ኤጀንሲ የተሰጠ የአቅራቢነት ማስረጃ አርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

3.     ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትንና እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋ ጨምሮ መሆኑን መገለጽ አለበት- የታክስ ሁኔታ ያልተገለፀ ከሆነ የቀረበው ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ታክስና ወጪ አካቶ እንደተሞላ ይቆጠራል።

4.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር 10,000 ብር (አስር ሺህ ብር) በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ፋይናንሺያል ኦርጅናል ሰነድ ፖስታ ውስጥ አብረው በማካተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5.     ተጫራቾች ይህ ጨረታ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በሀዋሳ ከተማ በገብርኤል ቤቴክርስቲያን ፊት ለፊት ከሚገኘው ዳዬ በንሳ ሕንጻ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 12 ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡

6.     ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 230 እስከ 430 ድረስ በቢሮ በተዘጋጀዉ ሳጥን አስገብተው ጨረታው በዕለቱ 500 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

7.     ተጫራቾት የሚያቀርቡት ዋጋ ቢያንስ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ እስከ 30 ቀናት ድረስ ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን መገንዘብ አለባቸው፡፡

8.     ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማለትም የፋይናንሺያል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በፖስታ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው

9.     ስርዝ ድልዝ ያለው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ከጨረታም ያሰርዛል፡፡

10. የመ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- በሲዳማ ክልል፣ ሀዋሳ ከተማ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው

ዳዬ በንሳ ሕንጻ 4ተኛ ፎቅ, ቢሮ ቁጥር 12, ስልክ ቁጥር 0943027779

 

ዳዬ በንሳ ቢዝነስ /የተ/የግ/ ማህበር

Save Tender