ለፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውል የሚዛን ጣቢያ የተመረጠበት ቦታ ላይ የመትከል ሥራ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 008/2017
ለፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውል የሚዛን ጣቢያ የተመረጠበት ቦታ ላይ የመትከል ሥራ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ከድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 28 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እንዲሁም የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሠነድ ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ፖስታ ኮፒ እና ኦርጅናል ለየብቻ በማዘጋጀትና በኤንቨሎፕ በማሸግ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 በተቀመጠ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond/ የዋጋ 2% ሲፒኦ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሠነድ በኤንቬሎፕ በማሸግ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተቀመጠ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 ይከፈታል የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በበዓል ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሜክሲኮ ወደ ልደታ ቤተክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ላይ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው፤
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 011-5-15-51-59
የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት
