የኢትዮጵያ ፖስታ ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቃ ማመላለሻ ዋግነር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግጨ /16/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፖስታ ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቃ ማመላለሻ ዋግነር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሱ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን ከድረ-ገፁ Web- site/አትመው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ከፋይነት የተመዘገቡ፤ የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ግዥ ከፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ከቴክኒካል የጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ሲኖርባቸው ፋይናንሻል ሰነድ ለብቻው በኤንቨሎፕ በማሸግ መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ቀኑ 6:30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ማለትም ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም በሠራተኞች ከበብ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሲፒኦ ሲያሰሩ ለፖስታ አገልግሎት ድርጅት /Ethiopian Postal Service Enterprise በሚል ያሰሩ።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር :-0911 95 45 37
ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ
