በጅማ ዞን የኦሞ ናዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በገጠር መንገድ ተደራሽነት ፕሮግራም የተሠሩ መንገዶች በመጎዳታቸው በ2017 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚጠገኑ መንገዶች የተለያዩ ማሽነሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል ፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በጅማ ዞን የኦሞ ናዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በገጠር መንገድ ተደራሽነት ፕሮግራም የተሠሩ መንገዶች በመጎዳታቸው በ2017 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚጠገኑ መንገዶች የተለያዩ ማሽነሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል ፡፡
ተፈላጊ ማሽነሪዎች
|
ተ/ቁ |
የማሽነሪው ዓይነት |
ብዛት |
ሞዴል |
ስሪት ዘመን |
የኪራይ ሁኔታ |
|
1 |
ኤክስካቫተር |
1 |
CAT 300 HP or above |
2015 |
በሰዓት |
|
2 |
ግሬደር |
1 |
CAT 140 HP or above |
2015 |
በሰዓት |
|
3 |
ሮለር |
1 |
14 TON or above |
2015 |
በሰዓት |
|
4 |
ዳምፕ ትራክ |
6 |
SINO 16 M3 |
2015 |
M3Per KM |
|
5 |
ፒካፕ |
1 |
TOYOTA |
2015 |
በ KM |
|
6 |
ሻወር ትራክ |
1 |
15,000 Litre |
2015 |
በወር |
|
7 |
ሎውቤድ |
1 |
----- |
2015 |
በወር |
ተፈላጊ መስፈርቶች
1. የማሽነሪ አከራይነት ፍቃድ ወይም በ Road Construction ( R.C.) ህጋዊ ፍቃድ ያለው ::
2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለና ፍቃድ ያሳደሰ ::
3. የቫት ተመዝጋቢ የሆነና መረጃ ማቅረብ የሚችል ::
4. ለጨረታው ማስከበሪያ CPO 200,000 ብር ማቅረብ የሚችል ::
5. ለሚወዳደርባቸው ማሽነሪዎች ቢያንስ 50 % የባለቤትነት ደብተር ወይም ሊብሬ ማቅረብ የሚችል ::
መስፈርቱን የምታሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት በማይመለስ 400 ብር በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን በተዘጋጀው ሰነድ ላይ የማሽነሪውን መረጃ እና ዋጋ በመሙላት ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒውን በመለየት እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድና CPO በአንድ ፖስታ ኦርጅናል አና ኮፒውን በመለየት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 20 ተከታታይ የሥራ ቀናት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን የጨረታው ሣጥን በ20ኛው ቀን 11፡00 ታሽጎ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል ፡፡
ማሳሰቢያ
1. በሠንጠረዥ ውስጥ ከተራ ቁጥር 1-7 ያሉትን ማሸነሪዎች ነጣጥሎ መወዳደር ከጨረታ ውጭ ያደርጋል ::
2. በገጠር መንገድ ግንባታና ጥገና ሥራ ልምድ ያለው ይበረታታል፡፡
3. መ/ቤቱ የተሻለ ዋጋ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር -- 09 17 60 00 60 / 0917053998 ይደውሉ ፡፡
በጅማ ዞን የኦሞ ናዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
