በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከዚህ በታች የተገለፁትን ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 0001/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከዚህ በታች የተገለፁትን ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
| NO. | Items | Quantity |
| Lot one | ||
| 1 | Double cabin pick up | 2 |
| 2 | Station wagon 9 seat hard top | 2 |
| 3 | Station wagon 7 seat | 3 |
| 4 | Station wagon v6 | 1 |
| 5 | Meat transporter truck | 2 |
| Lot two | ||
| 1 | Dump truck | 4 |
| 2 | Wheel loader | 1 |
| 3 | Excavator | 1 |
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች :-
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት/Tin Number/ ያላቸው
- ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸው የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት
- ማንኛውም ተጫራች የንግድ ፍቃዱን በማቅረብ ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ሆሳዕና በሚገኘው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የግዥና ዋጋ ጥናት ዳይሬክቶሬት በመቅረብ በየተሽከርካሪና ማሽነሪ አይነት የማይመለስ 100.00/አንድ መቶ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 20 ቀናት አየር ላይ ይውላል።
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው 20ኛ ቀን ከቀኑ 6.00 ሰዓት ድረስ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የግዥና ዋጋ ጥናት ዳይሬክቶሬት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው አየር ላይ መቆያው ጊዜ ባበቃበት ቀን 6.00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8.00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጨረታው በጋዜጣ የሚውልበት የመጨረሻ ቀን በዓል፣ቅዳሜ ወይም እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለሎት አንድ 1,000,000/አንድ ሚሊየን እና ለሎት ሁለት 1,000,000/አንድ ሚሊዮን ብር የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910928986 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት (ሆሳዕና)
✨ messages.ai_summary
Open tender for purchase of vehicles and machinery in two lots: Lot 1 includes pickups, station wagons, and a meat transporter truck; Lot 2 includes dump trucks, a wheel loader, and an excavator. Bidders must be registered suppliers with VAT, valid trade license, and tax clearance.
