Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን
  • Address ከራስ ሃይሉ መዝናኛ ማዕከል አጠገብ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ህንፃ ዋና ስራ አስፈፃሚ ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ በግራ ክንፍ በኩል ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118 69 38 76
  • Website
  • Deadline13 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 400.00 /አራት መቶ ብር/
  • opening dateበ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Categories Vehicles Rent , Vehicle

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት መጠቀሚያ የሚሆን በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለአንድ አመት ውል በማስገባት በኪራይ አገልግሎት መጠቀም ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ 01/2019

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት መጠቀሚያ የሚሆን በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለአንድ አመት ውል በማስገባት በኪራይ አገልግሎት መጠቀም ይፈልጋል።

ሎት 1:- 12 ሰው የሚይዝ ሚኒባስ እና 5 ሰው የሚይዝ አውቶሞቢል በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለአንድ አመት ውል በማስገባት በኪራይ መጠቀም ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መዳደር ይችላሉ።

1.      በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በጨረታ ላይ መካፈል የሚያስችል የገቢዎች ክሊራንስ፣ በግዥ ኤጀንሲ ድረ ገጽ/online/ተመዝጋቢ የሆኑ እና በጨረታ ሰነዱ ከፍል 3 ላይ በተቀመጠው ለእያንዳንዱ ሎት ዝርዝር መመዘኛ የሚያሟላ መሆን አለበት። የተሽከርካሪ ኪራይ በተመለከተ ቴክኒክ ምርመራ የተደረገልት፣ ሙሉ ኢንሹራንስ ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይመለስልን የማትሉት ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈልመግዛት ይኖርባቹዋል።

2.    ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት ብር 50,000.00 /ሀምሳ ሺ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3.    ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲያሰሩ የሚያሰሩበት ስም ADDIS KETEMA SUBCITY ADMINISTRATION CHIEF EXECUTIVE PURCHASING ADMINISTRATION SUPPORTIVE PROCESS OFFICE በሚል ስም በማዘጋጀት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4.    ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ማድረግ እንዲሁም እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

5.    ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ኦርጅናል በተጨማሪ ለእያንዳንዱ ኦርጂናል ሰነድ ኮፒ ጨረታ ሰነድ በማድረግ ከተሟላ ሰነድ ጋር ለየብቻ አያይዘው በማሸግ በፖስታው ላይ የተወዳደሩበትን ሎት እና ዘርፍ በጉልህ በሚታይ ሁኔታ በመፃፍ ማቅረብ ይኖርባቹዋል።

6.    ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሰውን ማስረጃዎች አማልተው በሰም በታሸገ አንድ /1/ ኦርጂናል እና አንድ /1/ ኮፒ በማድረግ የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን መድዓኒአለም ከግሩም ሆስፒታል ከፍ ብሎ ባለው አስተዳደሩ ጽ/ቤት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7.    አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ እንደተገለጸ የውል ማስከበሪያ 10% /ሲ.ፒ.ኦ/ ዋስትና በማስያዝ ውል መግባት ይኖርባቸዋል።

8.    ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ ላይ ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል። እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም።

9.    መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0118 69 38 76/0118 961750 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

አድራሻ፡- ከራስ ሃይሉ መዝናኛ ማዕከል አጠገብ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ህንፃ ዋና ስራ አስፈፃሚ ግዥ ቡድን 7ኛ ፎቅ በግራ ክንፍ በኩል

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን

Save Tender