በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ህትመት፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ልዩ ልዩ ዕቃዎች LCD Display ' የሬዲዮ እና ማስታወቂያዎች መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልገሎት ግልፅ ጨረታ 2/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ህትመት፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ልዩ ልዩ ዕቃዎች LCD Display ' የሬዲዮ እና ማስታወቂያዎች መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዕቃ አቅራቢነት ሊስት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ (Vat) ተጠቃሚ መሆናቸውን መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት 16/5/2017-ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የጨረታ ሰነድ በመ/ቤታችን ከፍያና ሂሳብ ዳሬከቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በየሎት ጨረታ ሰነድ ሽያጭ ላይ በሚገኘው መሰረት ማስያዝ ወይም ቢድ ቦንድ ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታውን ሰነዶች ዋጋ የሰጠበትን መስሪያ ቤታችን በሚያዘጋጀው ሰነድ መሰረት አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በማዘጋጀት በድምሩ በሁለት ፖስታ ለየብቻ ታሽጐ ባዘጋጀነው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡
- ጨረታው 30/5/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4.00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት በመ/ቤቱ ሚኒ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች በሙሉ ናሙና ወይም ስፔስፊኬሽን የተጠየቀበት ማቅረብ አለበት። ለማቅረብ አስቸጋሪ የሆኑትን ዕቃዎች በአካል ማሣየት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ መ/ቤቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለበት፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከሚከፈትበት ዕለት ጀምሮ ስልሳ የስራ ቀናት ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የፋይናንሻል ዋጋ መሙላት የሚቻለው በተቋሙ ባዘጋጀው ሰነድ መሰረት ብቻ ነው፡፡
ማሳሰቢያ
የሚገዛው ዕቃ ዝርዝር ከዚህ የጨረታ ሠነድ ጋር የተያያዘ ስለሆነ በተዘጋጀው የዕቃ ዝርዝር መሰረት በእያንዳንዱ ተራ ቁጥር የምታቀርቡበትን የአንዱን እና ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ እንዲገለጽ እና ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ፍላሽ ይዘው በመምጣት በሶፍት ኮፒ እንዲወስዱ እናሳስባለን፡፡
አድራሻችን ፡- አዲሱ ገበያ ሸገር መናፈሻ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር ፡- 011-1-57-58-43
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
