Tender Detail

Tender Details

  • Company Nefas Silk Polytechnic College (የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
  • Address ጎተራ ኦይል ሊቢያ ዴፖ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114-70-70-78
  • Website
  • Deadline03 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Maintenance And Repair

ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የማሽን ጥገና እና የቢሮ እቃዎች ጥገና እና የኮሌጁን መሰረተ ልማት የሚሰሩ ሥራዎችና የተለያዩ ጥገናዎችን ግዥ ለ2017 በጀት ዓመት በሁለተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 4/2017 .

 

ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የማሽን ጥገና እና የቢሮ እቃዎች ጥገና እና የኮሌጁን መሰረተ ልማት የሚሰሩ ሥራዎችና የተለያዩ ጥገናዎችን ግዥ 2017 በጀት ዓመት በሁለተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

                ሎት                                           የግዥ

1. የኮሌጁን መሰረተ ልማት የሚሰሩ ሥራዎች - የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር)

2. የማሽን እና የቢሮ እቃዎች ጥገና            - የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር )

3. ለከተማ ግብርና የሚውሉ ግብአቶች       - የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር )

በዚህም መሰረት ፡-

  1. ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች የግብር ከፋይ ቁጥር (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  4. ጨረታው 7ኛው የሥራ ቀን 400 ሰዓት ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን የግዥ ዓይነት (ሎቶች) ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ጋራንቲ Nifas Silk poly Technic Collage (ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ) በሚል በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መውሰድ ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒውን እና ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ ለመ//// ቢሮ ቁጥር 101 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተም እና ፊርማ አድርጎ የማያቀርብ ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ናሙና ማቅረብ አይቻልም፡፡ ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ / ተጫራች ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
  10. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ - አዲስ አበባ ጎተራ ኦይል ሊቢያ ዴፖ አጠገብ

ስልክ ቁጥር ፡- 0114-70-70-78

 

 

የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

 

Save Tender