በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከ/ወ/5 ጤና ጣቢያ የ2017 በጀት 2ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ ለጤና ጣቢያው ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከ/ወ/5 ጤና ጣቢያ የ2017 በጀት 2ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ ለጤና ጣቢያው ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1- የጽህፈት መሳሪያ፣
ሎት 2- የፅዳት እቃ፣
ሎት 3- የደንብ ልብስ፣
ሎት 4- ቋሚ እቃዎች፣
ሎት 5- መድሃኒትና የህክምና እቃዎች (Medical Equipment)
- በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ከላይ ከሎት -1-5 ለተጠቀሱት ዕቃዎች አግባብነት ያለው
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም፤
- ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና በዘርፉ የተሰማሩ፤
- በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፤
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በኮ/ቀ/ክ/ከ/ ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ግ/ን/አስተዳደር በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መስከበሪያ ዋስትና ከሎት 1-4፤ 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) እንዲሁም ለሎት 5፤ 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በማስያዝ በመስሪያ ቤታችን (በወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ስም) በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች የሚያቀርቡበትን የአንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ በመግለፅ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኢንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውንና የጨረታውን አይነት በመጥቀስ ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ግ/ን/አስ የስራ ሂደት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ለህክምና ዕቃዎች የአቅራቢነት ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሺያል ሰነድ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 3፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በ3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ 5 ጤና ጣቢያ በሁለገብ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- የህክምና ዕቃዎች ተጫራቾች ቴክኒካል ኦርጅናል ፤ ቴክኒካል ኮፒ፤ ፋይናንሺያል ኦሪጅናል፤ ፋይናሺያል ኮፒ ሰነዶች ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ ለጤና ጣቢያው እንደ ትዕዛዙ (Specification) አይነት እቃዎቹን ጤና ጣቢያው ድረስ የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙና ማቅረብ ለሚቻልባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡ናሙና ላልቀረበባቸው ዕቃዎች ተጫራቹ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ልዩ ስሙ ከኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ ከፍ ብሎ (72 ሰባራ ድልድይ)
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 011-8-33-85-25
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 ጤና ጣቢያ
