የአቃቂ ቤዝክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ የአዋጭነት ጥናት የምክር አገልግሎት በአገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- አቤሜኢ/ሰቼማ/ግጬ/2017/002
የአቃቂ ቤዝክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ የአዋጭነት ጥናት የምክር አገልግሎት በአገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የግብር መክፈያ ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥና በግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ቅጂ፤ አግባብ ያለው በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ ቅጂውን፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና የግብር መክፈያ መለያ ሰርተፍኬት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በአቃቂ ቤዝከ ሜታል ኢንዱስትሪ ስም ሒሳብ ቁጥር 1000014630906 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ኢንዱስትሪያችን በመቅረብ ከግዥ ክፍል ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በCPO ወይም bank guarantee ወይም Cash ቢያንስ ለ88 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት በ8፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 1ኛ ወለል ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 22 ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
- ቴክኒካልና ፋይናንሻል በሁለት ኤንቨሎፕ አሽጎ ዋናውና ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ ዘወትር በስራ ሰዓት በከፍሉ በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ ፡- ከአ.አ ወደ ዱከም መሄጃ መንገድ ላይ ከሚገኘው ገላን ከተማ ሳይደርስ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የፍተሻ ጣቢያ (ኬላ) አጠገብ ከASTCO FOOD COMPLEX በቀኝ በኩል ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡
በተጨማሪ መረጃ ፡- ስልክ ቁጥር 0114340409/0114350608
በኢትዮ ኢንጂነሪግ ግሩፕ አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ
