Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa City Administration Public Recreational Areas Corporation (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115572949
  • Websitehttps://aacaprac.gov.et/?lang=ahm
  • Deadline21 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Maintenance And Repair

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከታች የተገለጹትን አገልግሎቶች ውል በማሰር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስራትና እና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ፡- 47/2017

 

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከታች የተገለጹትን

ሎት 1 - የውሃ ቦቲ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመግዛት የአንድ አመት ውል በማሰር፣

ሎት 2 - ለኤቨንት የሚያስፈልጉ የልጆች መጫወቻን ለመከራየት የአንድ አመት ውል በማሰር፤

ሎት 3- የችግኝ ጣቢያ የሚሆን ግሪንሼድ ለመግዛት፤

ሎት 4 - ለችግኝ ጣቢያ የሚሆን የስንደዶ ሳር ለመግዛት፤

ሎት 5 - የኮምፒውተር፣ ፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ጥገና ስራ ለአንድ አመት ውል በማሰር፤

ሎት 6 - የተለያዩ ማሽነሪዎች (ጄኔሬተሮች፣ ፓምፖች፣ ፋውንቴኖች) ጥገና፣ ቢሮዎችን ቀለም መቀባትና የቢሮ ፈርኒቸሮችን መጠገን ስራ ውል በማሰር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስራትና እና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ተጋብዘዋል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና ስለግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ (Clearance) ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ለውሃ ቦቴ ትራንፖርት አገልግሎት 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) ሲሆን ለሌሎቹ ሎቶች ደግሞ 20,000 (ሀያ ሺህ ብር ብቻ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ በህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ጊቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር ተከታታይ የስራ ቀን ከጠዋቱ 230 እስከ 1130 ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ዶክመንት ለብቻ እና ቴክኒካል ዶክመንት ለብቻ በማሸግ እና ሁለቱንም ለየብቻ ኮፒ በማድረግ በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት 10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በኃላ ባለው 11ኛው ቀን 400 ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን 400 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን 430 ሰዓት ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ግቢ በግዥና ንብረት ዳይሬክትሬት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ሰኞ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7. ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ስልከ ቁጥር፡- 011-5-57-29-17/ +251-7-03-61-44-58 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች አስተዳደር ኮርፖሬሽን

 

Save Tender