ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ መንግሥታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅት ሲሆን በበጀት ዓመቱ ዕቅድ መሠረት በቁጥር 100,000 የሚሆኑ የእንሰት ችግኞችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ መንግሥታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅት ሲሆን በበጀት ዓመቱ ዕቅድ መሠረት በቁጥር 100,000 የሚሆኑ የእንሰት ችግኞችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የእንሰት ችግኞቹ ዓይነት ፡-
- ለአካባቢው አየር ተስማሚ የሆነ (ከሚችሌ ግሪሳና ከአምባ ቡላ እንዲሁም ከዳማ ስኬ ማቅረብ የሚችል)
- ገንትቾ ቶረልቶ የመሳሰሉት ለተከላ የደረሱ (ርዝሙቱ ከ60-70 ሳ.ሜ፣ ውፍረት ከ7- 10ሳ.ሜትር) ችግኞችን ማቅረብ የሚችል
- በራሱ ትራንስፖርት በየቀበሌዎች ልማት ጣቢያ ድረስ ማቅረብ የሚችል።
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚችሉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በእንሰት እና እንሰት ተዋፅዖ አቅራቢነት የንግድ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑ የታደሰ የንግድና የዋና ምዝገባ ፈቃዳቸውን፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በጨረታ እንዲሳተፉ ለዘመኑ በጀት ዓመት ብቻ የሚያገለግል የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚል መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- መስፈርቶቹን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት (7) የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር ጠዋት ከ2፡30–6፡30 እና ከሰዓት ከ7፡30–11፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 400.00 ብር (አራት መቶ ብር) በፕሮጀክቱ ስም ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ገቢ በማድረግና የማስረጃዎቻቸውን ኦርጅናል ይዘው በመቅረብና በመመዝገብ ኮፒውን በማስያዝና ደረሰኝ በመቀበል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች አንድ ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ሰነዶችን እያንዳንዳቸውን በስም በታሸገ ኢንቬሎፕ በማድረግ አንድ ላይ በማሸግ በሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር ) ሲፒኦ በሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ስም አሠርተው ከኦሪጅናሉ የጨረታ ሰነድ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰባተኛው ቀን በኋላ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ2፡30 እስከ 6፡00 ድረስ ለዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ የሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-331-0049 / 046-331-3145/2071 ዘወትር በስራ ሰዓት ደውሎ መጠየቅና መረዳት ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ዲላ ከተማ ከዲላይት ኢንተርናሽናል ሆቴል 150 ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል።
ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ
