Tender Detail

Tender Details

  • Company ETHIOPIAN LOTTERY SERVICE (የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት)
  • Address ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-126-78-16
  • Website
  • Deadline04 Mar 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Ict And Telecom Service

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት ለኮምፒውተሮች፣ ለሰርቨሮች እና ተዛማጅ ለሆኑ ዕቃዎች አገልግሎት የሚውል አንቲቫይረስ አቅራቢ ድርጅቶችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ኢሎአ/004/2017

 

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት 2017 በጀት ዓመት ለኮምፒውተሮች፣ ለሰርቨሮች እና ተዛማጅ ለሆኑ ዕቃዎች አገልግሎት የሚውል አንቲቫይረስ አቅራቢ ድርጅቶችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ የካቲት 25 ቀን 2017 . ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመፈልና በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፤

ተጫረቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባን ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ አድርገው ዋናውን ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው። ተጫራቾች በስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት /ቤት ውስጥ የተደራጁ ህጋዊ ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት በጨረታው ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ያለባቸው ከአደራጃቸው ተቋም የሚያቀርቡት የድጋፍ ደብዳቤ ውስጥ መካተት ያለባቸው ሁኔታዎች የሚወዳደሩበትን ተቋም ስም፣ የሚወዳደሩበትን የግዥ ዓይነት፣ የጨረታ ቁጥር እና የጨረታ ማስከበሪያውን የገንዘብ መጠን በግልጽ በአሃዝና በፊደል የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶችን የቴኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶችን የያዘ አንድ ዋና እና አንድ ቅጂ ለየብቻው በፖስታ በማድረግና በፅሁፍ በመለየት የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ሊራንስ፣ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስ ረቀት፣ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገባበት ቅፅ ሞልታችሁ ማህተምና ፊርማ አድርጋችሁ የመጫረቻ ሰነዶቻችሁን አሟልታችሁ በማቅረብና የጨረታ ማስከበሪያውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ እስከ የካቲት 25 ቀን 2017 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ በዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት የካቲት 25 ቀን 2017 ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና /ቤት ይከፈታል፡፡ አገልግሎቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-78-16 ደው መረዳት ይቻላል፡፡

 

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት

 

Save Tender