Tender Detail

Tender Details

  • Company Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)
  • Address Bole Road, behind Dembel City Center, Seid Yassin Building., addis ababa,Ethiopia, Phone: 011-1-569992
  • Websitehttps://commercialnominees.com/
  • Deadline15 Sep 2019, 4:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 100.00
  • opening date መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡30
  • Categories Ict Equipment'S And Its Accessories , Ict And Telecom Service , Cctv Camera

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል/ማህበር ለድርጅታችን የሥራ አገልግሎት ላይ መዋል የሚችሉ፡-


የጨረታ ማስታወቂያ

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል/ማህበር ለድርጅታችን የሥራ አገልግሎት ላይ መዋል የሚችሉ፡-

ሎት 1፡- የተለያዩ የኔትዎርከ ዕቃዎች (Different Network Devices) እንዲሁም

ሎት 2:- CCTV Surveilance System, Laptop Computer, Desktop Computer, Heavy duty Copier, Printer, projector

ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ኤንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ከፍል ብር 100.00 በመከፈል ከሰኞ እስከ ዓርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 ከሰዓት 7፡00-11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ ብር100,000 ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶከመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡

ተጫራቾች የመጫረቻ ዶከመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡

ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ያሸነፈው ተጫራች የዕቃዎች ርክክብ የሚደረግበት ቦታ ገርጂ የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር 011-1-569992

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ

Save Tender