Tender Detail

Tender Details


የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትም/ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት የWFP/አለም ምግብ ፕሮግራም/በጀት በመጠቀም የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ማለትም፡-


የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር 01 ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትም/ቢሮ 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትም/ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት የWFP/አለም ምግብ ፕሮግራም/በጀት በመጠቀ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ማለትም፡-

1.      ላፕቶፕ Core i7 ብዛት 2/ሁለት/ በቁጥር

2.    ላፕቶፕ Core i5 ብዛት 17/አስራ ሰባት/ በቁጥር

3.    Tablet ብዛት 3/ሦስት/ በቁጥር

4.    Desktop Computer ብዛት 10/አሥር/ በቁጥር

5.    Printer ብዛት 17/አሥራ ሰባት/ በቁጥር

ግዥ ለመፈጸም በሥራ መስክ የተሰማሩ የንግድ ድርጅቶችን ለማወዳደር ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች

1.      በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሴርቴፍከት፣ የዘመኑን የግብር ግዴታውን የተወጣ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበት መረጃ ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

2.    ተጫራቾች ትምህርት ቢሮ ቁጥር 18 በመቅረብ ለሥራው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘውትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።

3.    የፋይናንሻል ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ ለየብቻ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ አሽጎ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቢሮ ቁጥር 18 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4.    ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ በተጫራቾች መመሪያ ወይም ሰነድ ላይ በሚገለፀው መሠረት ጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው።

5.    ጨረታው ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት ሰነዱ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ገብቶ ወድያውኑ ታሽጎ ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።

6.    መ/ቤቱ በጨረታው ላይ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0467752359 መጠየቅ ይችላሉ።

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትም/ቢሮ ጂንካ

Save Tender