የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኦክስጅን፣ የካርቦን ዳይኦክሳይድ እና አሴቲለን ጋዝ ሙሌት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን አወዳድሮ በረጅም ጊዜ ውል ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥC SSNT-T528
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኦክስጅን፣ የካርቦን ዳይኦክሳይድ እና አሴቲለን ጋዝ ሙሌት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን አወዳድሮ በረጅም ጊዜ ውል ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከላይ በተጠቀሰው አገልግሎት ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ ፣ የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት TIN (የግብር መለያ ቁጥር) ያለውና በዘርፉ እየሰራ ያለ ማንኛውም ተቋም በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T528 በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጂውን (Deposit Slip Copy) ፤ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው ባንክ ጋራንቲ (unconditional bank guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል::
ተጫራቾች በጨረታው ሠነድ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው:: የጨረታው ተጫራቾች በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ፕሮኪውርመንት እና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት ክፍል
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በስልክ ቁጥር 011 517 8025/4028
ኢ-ሜይል : KidistTa@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ
የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
