Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት በተያዘለት የመንግስት በጀት ለሆስፒታሉ መገልገያ የሚሆኑ የላውንደሪ የልብስ እጥበትና የኦከስጅን ጋዝ አቅርቦት ፤ የሲሊንደር እጥበትና ጥገና አገልግሎት ዓመታዊ ውል/ ፣ ህትመት ፣ የጽዳት ዕቃዎች እና የቢሮ አላቂ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የግልጽ ጨረታ ቁጥር 02/ 2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል 2018 በጀት ዓመት በተያዘለት የመንግስት በጀት ለሆስፒታሉ መገልገያ የሚሆኑ የላውንደሪ የልብስ እጥበትና የኦከስጅን ጋዝ አቅርቦት የሲሊንደር እጥበትና ጥገና አገልግሎት ዓመታዊ ውል/ ህትመት የጽዳት ዕቃዎች እና የቢሮ አላቂ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

1. የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት የታደሰ ንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታከስ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ከገቢዎች በጨረታ እንዲሳተፉ የተገለፀበት ደብዳቤ ያላቸው እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ እና በዘርፉ የተሰማሩ የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው:: በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ሰነድ በነፃ ለሚወስዱ ማህበራት በዘርፉ ስለመደራጀታቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

2. ተጫራቶች ከላይ የተዘረዘሩ የእቃ ወይም አገልግሎት አይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመከፈል ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 1 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሆስፒታሉ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

3.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1. የላውንደሪ የልብስ እጥበት ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/

ሎት 2. የህትመት ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር)

ሎት 3. የቢሮ አላቂ ዕቃዎች ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)

ሎት 4 የጽዳት ዕቃዎች ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)

ሎት 5. የኦክስጅን ጋዝ አቅርቦት የሲሊንደር እጥበትና ጥገና አገልግሎት ብር 10,000.00(አስር ሺህ ብር)

ሎት 6. የሰው መድሀኒት እና የህከምና መርጃ መሳሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO "ለጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል" ተብሎ በማዘጋጀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘጋጀው ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ ብቻ በመሙላት የድርጅታቸውን ማኅተምና ፊርማ አኑረው ፋይናሻል ኮፒ 1 ቴክኒካል ኮፒ 1 ፋይናሺያል ኦርጅናል 1 እና ቴክኒካል ኮፒ 1 በድምሩ 4 ፖስታ በማድረግ ዘወትር በስራ ቀንና ሰአት ከጠዋቱ 230 – 1130 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም ::

5. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ከጠዋቱ 430 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ባይገኙ ጨረታው ከመከፈት አያግደውም፡፡ ከኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንዲሁም ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡

7. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች ያለምንም አቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የእቃ ከምችት ያለውና የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% ለውል ማስከበሪያነት አስይዞ ተገቢውን ውል በመፈጸም እቃዎቹን በሆስፒታሉ ግቢ ንብረት ከፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

8. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ - አቃቂ ቃሊቲ /ከተማ ወረዳ 1 ወይም ልዩ ስሙ ጥምቀተ ባህር ወይም አቃቂ መሿለኪያ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ- ስልክ 0924777840 በስራ ሰአት መደወል ይችላል::

የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል

Save Tender