በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬድዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለድሬድዋ መልካ ጀብዱ የመንገድ ስራ ፕሮጀክት ለስራ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተጠቀሰውን የኮንስትራክሽን መሳሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል ፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬድዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለድሬድዋ መልካ ጀብዱ የመንገድ ስራ ፕሮጀክት ለስራ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተጠቀሰውን የኮንስትራክሽን መሳሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል ፡፡
|
ተ.ቁ |
የመሣሪያው ዓይነት |
ብዛት |
|
1 |
ቢትመን ድስትሪቢውተር |
1 |
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ የኮንስትራክሽን መሳሪያ አከራይ ድርጅት የሆነ ማሟላት ያለባችሁ መስፈርት እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
- የባለቤትነት መታወቂያ /ሊብሬ/ ያለው ወይም ህጋዊ ውክልና
- አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆን ይኖርበታል፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው/ያላት፣
- የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት፣
- በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ፣
- የሶስተኛ ወገን ሽፋን የሚያቀርብ፣
- ነዳጅ እንዲሁም የጥገና፣ የሹፌር ደመወዝና አበል በአከራይ ይሸፈናል፡፡
- ከላይ ለተዘረዘሩት የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች በሰዓት የሚከራይበትን ዋጋ ድሬድዋ መንገድ ጥገና ድስትሪክት ከሚገኘው ቢሮችን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነድ በመውሰድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
- በድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ስር ባሉ የስራ ቦታዎች መስራት የሚፈልግ፣
- አሸናፊ ተጫራቾች የቴክኒክ ምርመራውን ካለፈ ውል በመፈፀም ወዲያውኑ ወደ ሥራ መሰማራት አለበት፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ድሬድዋ በሚገኘው የመ/ቤቱ ዋና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ዕለት የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0929063249 /0919008017 ደወሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬድዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
