የሸካ ዞን ማሻ ማረሚያ ተቋም በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ቀለብ እህል፤ ጥራጥሬና ሸቀጣሸቀጥ ከሚያዝያ 1/2017 ዓም እስከ ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም ለ120 ቀናት ከሚያቀርቡ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ፣ አቅራቢ ነጋዴዎችና ማህበራት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የሸካ ዞን ማሻ ማረሚያ ተቋም በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ቀለብ እህል፤ ጥራጥሬና ሸቀጣሸቀጥ ከሚያዝያ 1/2017 ዓም እስከ ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም ለ120 ቀናት ከሚያቀርቡ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ፣ አቅራቢ ነጋዴዎችና ማህበራት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች ፡-
1ኛ/ በየዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
2ኛ/ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
3ኛ/ የጨረታው ተወዳዳሪዎች ለጨረታው ማስከበሪያ ለእህል ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) እና ለጥራጥሬና ሸቀጣሸቀጥ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በጥሬ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 3 የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችል፤
4ኛ/ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ያለውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5ኛ/ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
6ኛ/ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ይከፈታል።
7ኛ/ የጨረታው አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ዕቃዎችን አጓጉዞ በራሱ ወጭ ለማሻ ማ/ተቋም ማስረከብ የሚችል፡፡
8ኛ/ ሸቀጣሸቀጥ እና እህል ተጫራቾች አሁን ባቀረቡት ዋጋ ለ4 ተከታታይ ወር ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን በመሀሉ የድርድር ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፡፡
9ኛ/ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% ለማስያዝ ፈቃደኛ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
10ኛ/ ተጫራቾች ህጋዊ መጋዘን እንዳላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
11ኛ/ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
የሸካ ዞን ማሻ ማረሚያ ተቋም
