የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚገለገልባቸውን ተሸከርካሪዎች በሙሉ GPS ማስገጠም ይፈልጋል፡፡
የተሽከርካሪ የGPS ገጠማ ግዥ ለመፈጸም
የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NEBE/NCB/09/2017
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚገለገልባቸውን ተሸከርካሪዎች በሙሉ GPS ማስገጠም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርበታል።
-
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ድረስ የማይመለስ 200.00 (ብር ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከቦርዱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 107 የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተበሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ፣ ታክስ ክሊራንስ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ60 ቀናት ብቻ ነው::
-
ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ ማኖር ይገባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያነት ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በሲፒኦ፣ በካሽ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
-
ጨረታው ሚያዚያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት በ8፡30 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዢ የስራ ክፍል ይከፈታል፡፡
-
በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መከፈት እያስተጓጉለውም ::
-
ቦርዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
-
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ ካለውና ዋና መ/ቤት በአካል መቅረብ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻችን፡- ቦሌ ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር: +251 115153468
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ
