ፀደይ ባንክ አ.ማ Vulnerability Assessment and Penetration Testing Solution Acquisition ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ፀደይ ባንክ /አ.ማ/
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/0014/2017
ፀደይ ባንክ አ.ማ Vulnerability Assessment and Penetration Testing Solution Acquisition ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት /ነጋዴ/ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን::
-
የ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር መክፈያ ሰርቲፊኬት፣ የታክስ ክሊራንስና የብቃት ማረጋገጫ ሊኖራቸዉ ይገባል፡፡ ቴክኒካል ዶክሜንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ዶክሜንቱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
-
ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500 ሺህ የሚበልጥ ከሆነ ብር 500 ሺህ በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ90 ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል:: ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አ.ማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም ::
-
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወለል ላይ በመክፈል 7ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 704 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ::
-
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ሚያዝያ 07 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ለገሀር አመልድ ህንፃ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 7ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
-
የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም::
-
ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አዲስ አበባ ለገሃር
ስልክ ቁጥር 0115583187/0115581699
ፀደይ ባንክ አ.ማ
