አዲስ ፋና ጠቅላላ ሸቀጣ ሸቀጥና ሆቴሎች ንግድ አክሲዮን ማህበር በግዥ ተረክቦ ለምርት ግብዓት ሲጠቀምባቸው ከቆዩ የምርት ገብዓቶች መካከል የፓኪስታን ሸራ ፤ ፖሊስተር ታፍት እና ፉሌር ከቨሪንግ የተባሉ የምርት ግብዓቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ልዩ ልዩ የምርት ግብዓቶችን ለመሸጥ የወጣ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ ፋና ጠቅላላ ሸቀጣ ሸቀጥና ሆቴሎች ንግድ አክሲዮን ማህበር በግዥ ተረክቦ ለምርት ግብዓት ሲጠቀምባቸው ከቆዩ የምርት ገብዓቶች መካከል
-
የፓኪስታን ሸራ
-
ፖሊስተር ታፍት
-
ፉሌር ከቨሪንግ የተባሉ የምርት ግብዓቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ ነጋዴዎች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ዝርዝር ለማወቅ መረጃ ከድርጅቱ ዋና መ/ቤት ራስ መኮንን ድልድይ አጠገብ በሚገኘው ኢትሆፍ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 – 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በመክፈል መግዛትና መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፤ የሚሸጠውን ዕቃ ለማየት የጨረታ ሰነድ ከገዙ በኋላ ጦር ኃይሎች በሚገኘው አንበሳ ማምረቻ ማዕከል በአካል በመሄድ መመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር :- 0911-41-56-30 /0966-61-61-61
አዲስ ፋና ጠቅላላ ሸቀጣሸቀጥና ሆቴሎች ንግድ አክሲዮን ማህበር
