ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2017
ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
- ያገለገሉ መካኒካል ማሽንስና ስፔር
- ያገለገሉ የኤሌክትሪክ ሞተሮች
- ልዩ ልዩ ዕቃዎች
- የፈርነስ ፍሳሽ ባለበት ሁኔታ በሊትር
- የተቆራረጡ ብረታ ብረቶች
- ብሮንዝ
በመሆኑም ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በሙሉ አንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 Iሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከኩባንያው የምርት ሽያጭ ቢሮ መግዛት እና እቃዎቹን ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጓቸውን እቃዎች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የእያንዳንዱን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በግልፅ ሞልተው፤ ሙሉ ስማቸውንና አድራሻቸውን ጽፈው ከፈረሙበት በኋላ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሽያጭ ቢሮ ፊት ለፊት ባለው የጥበቃ በር ቁጥር 2 ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ሣጥኑ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡05 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ጨረታው ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡20 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፡- ንብረት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ
ስልክ ቁጥር 011-442-15-55/234 ወይም 0943880372 መጠየቅ ይቻላል፡፡
ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
