በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሕፃናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት የገነተ ኢየሱስ ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለተማሪዎች የሚሰጥ የንፅህና መጠበቂያ Rose ሞዴስ 3,200 /ሶስት ሺህ ሁለት መቶ/ አጫርቶ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሕፃናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት የገነተ ኢየሱስ ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለተማሪዎች የሚሰጥ የንፅህና መጠበቂያ Rose ሞዴስ 3,200 /ሶስት ሺህ ሁለት መቶ/ አጫርቶ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች:-
- በጨረታው ለመወዳደር የሚያበቃቸው በሥራ ዘርፉ ፈቃድ ያላቸውና የታደሰ የዘመኑ ንግድ ስራ ፈቃድ መኖር አለባቸው::
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከድርጅታችን መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 2% በባንከ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቶች የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአምስት /5/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በሚያስገቡበት ጊዜ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው የንፅህና መጠበቂያ Rose ሞዴስ አይነት አንድ ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
- ጨረታው አሸናፊ ድርጅት ለተማሪዎች የሚሰጥ የንፅህና መጠበቂያ Rose ሞዴስ ውል ከተፈራረመበት ዕለት ጀምሮ በ2 /ሁለት/ ቀናት ውስጥ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም በራሱ ትራንስፖርት ማስተባበሪያ ጽ/ቤታችን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የሞዴሶቹ ብዛት በሚሰጠው ዋጋ መሰረት ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል፡፡
- ጨረታው ሚያዚያ/3/2017 ዓ.ም. 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማሪጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1-14-29-48 መጠየቅ ይቻላል፡፡
- CPO የሚሰራበት ስም EOC-CFAO Genete Eyesus Child and Family Development Program Coordination Office በሚል ይሆናል፡፡
አድራሻ
በየካ ክ/ከ ወረዳ 1 ከገነተ ኢየሱስ ቤተከርስቲያን ዝቅ ብሎ ወደ ፈረንሣይ ኤምባሲ በሚወስደው መንገድ ሚያዚያ 23 ት/ቤት ሳይደርሱ ከሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤታችን በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ሕፃናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት
