የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ ቅ/ጽ/ቤት የሚገኘውን ጎመን ዘር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ጎመን ዘር ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ‑ኢምዘደውአ/
ጨሸ/03ሠነድ/2017
የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ ቅ/ጽ/ቤት የሚገኘውን ጎመን ዘር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ስለሚፈልግ፡-
- ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ እና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፤
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ CPO በኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከ11፡00 ሰዓት በፊት) በዋናው መ/ቤት የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 04 የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የተገለፀውን መጠን ጎመን ዘር መጫረት ይችላል፤
- ማንኛውም ተጫራች ጎመን ዘር በአርዳይታ ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት አይቶ መጫረት አለበት፡፡ ይህን ሳያደርግ ዋጋ ቢያቀርብ ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- የጎመን ዘር መጠን በዚህ ጨረታ ሠነድ ላይ ከተገለፀው መጠን ሊያንስ ይችላል፡፡
- ዋጋውን በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፍ ጽ/ቤት አዳራሽ እና ከላይ በተጠቀሱት ቅ/ጽ/ቤቶች ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 011 6 18 61 25
የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ
