ዋንዛ ፈርኒሺንግ ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ከታች የተዘረዘሩትን ለእንጨት ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጣውላዎችን በግልፅ ጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ቁጥር ዋ/ፌ/ኢ/ጣግጨ/03/2017
- ዋንዛ ፈርኒሺንግ ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ከታች የተዘረዘሩትን ለእንጨት ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጣውላዎችን በግልፅ ጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የጣውላ አይነት /Timber Type |
ዝርዝር መግለጫ /Spacification |
|
1 |
ቀረሮ |
ቁመት፡ 2.80 – 300 ሜትር ስፋት፡ ከ20 ሴሜ በላይ ውፍረት፡ ከ5 ሴሜ በላይ |
|
2 |
ዋንዛ |
ቁመት፡ 2.80 – 300 ሜትር ስፋት፡ ከ20 ሴሜ በላይ ውፍረት፡ ከ5 ሴሜ በላይ |
- በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፤
- ተጫራቾች በዘርፉ መወዳደር የሚስችል የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) እና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ከጨረታ መወዳደሪያ ኦሪጂናል ሰነድ ጋር በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ዋንዛ ፈርኒሺንግ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ወይም Wanza Furnishing Industry Private Limited Company ስም ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሰሚት ፔፕሲ ፋብሪካ በስተጀርባ በሚገኘው በድርጅቱ አንደኛ ፎቅ የግዥ መምሪያ ክፍል እና ሐዋሳ ሞቢል ሰፈር ህይወት ብርሃን ቸርች ወረድ ብሎ ዳሽን ባንክ አጠገብ በሚገኘው ዋንዛ ፈርኒሺንግስ ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በመቅረብ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጣውላ አይነት በግልፅ ለይተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ እስከ ግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከታች በተገለፀው አድራሻ ጠዋት 4፡00 ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤
- ጨረታው ግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 4:30 ከታች በተገለፀው አድራሻና ቦታ ይከፈታል፣
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ ሰነዱ የሚገኝበት አድራሻ፡-ዋናው መ/ቤት አዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክ/ከ ወረዳ 10 የቤት ቁጥር አዲስ ሰሚት ከፔፕሲ ፋብሪካ በስተጀርባ በሚገኘው የዋንዛ ፈርኒሺንግ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አንደኛ ፎቅ ግዥ መምሪያ ቢሮ እና ሐዋሳ ሞቢል ሰፈር ህይወት ብርሃን ቸርች ወረድ ብሎ ዳሽን ባንክ አጠገብ በሚገኘው ዋንዛ ፈርኒሺንግስ ፋይናንስ ቢሮ ፣
ስልክ ቁጥር 0911 926283
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋንዛ ፈርኒሺንግ ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
