ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ያገለገሉ የእንጨት ፓሌቶች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ አስቸኳይ ያገለገሉ ፓሌቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
| የጨረታ ቁጥር | NFR 004-2026 |
| የጨረታ ዕቃዎች መመልከቻ ጊዜ | ከሰኞ ነሃሴ 25 እስከ ማክሰኞ 26/2018 ዓ.ም |
| የጨረታ ሰነድ መግዣ ጊዜ | ከሰኞ ነሃሴ 25 እስከ ማክሰኞ 26/2018 ዓ.ም |
| የጨረታ ዕቃዎች መገኛ ቦታ | አይሲሲ መጋዘን |
| የጨረታ ሰነድ መሸጫ ቦታ | ዩኒሴፍ አይሲሲ መጋዘን |
| የጨረታ ሰነድ መመለሻ የመጨረሻ ጊዜ | ሃሙስ ነሀሴ 28 2018 ዓ.ም፣ ከቀኑ 10:00 ሰዓት በፊት |
| የጨረታ ሰነድ መመለሻ ቦታ | ዩኒሴፍ አይሲሲ መጋዘን |
| የፓሌቶች ብዛት | ከ2000 በላይ |
ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ያገለገሉ የእንጨት ፓሌቶች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የመጫረት ፍላጎት ያላችሁ ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ፡፡ በተጨማሪም በጨረታው ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ ብር) የባንክ ሲፒኦ በማስያዝ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡– ከላይ ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን እየገለፅን የእቃው መገኛ ቦታ አይሲሲ መጋዘን በሚገኙት የድርጅቱ መጋዘኖች መሆኑን እንገልፃለን።
ዩኒሴፍ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን፡– አይሲሲ መጋዘን
ደብረ ዘይት መንገድ ከጎተራ ወደ ስቴዲየም በሚወስደው መንገድ ከሰናይ ክሊኒክ አለፍ ብሎ ከቀድሞ ላንቻ በቀኝ በኩል ታጥፎ 500ሜትር ርቀት ላይ ያገኙናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911 119447, 0938 607109 ወይም 0912 464149 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
