Tender Detail

Tender Details

  • Company Habesha Cement
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline18 Sep 2026, 3:38 PM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document Price
  • opening date2026-09-02 15:38:00
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ በዋናው መስሪያ ቤት ሲጠቀምባቸው የነበሩ በመጠኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ሞተር ሳይክሎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

HCSC/M/NCB/-0001/2018

ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ በዋናው መስሪያ ቤት ሲጠቀምባቸው የነበሩ በመጠኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ሞተር ሳይክሎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ የነዋሪነት መታወቂያ እንዲሁም ቋሚ አድራሻ ያላቸው ግለሰቦች እንዲሁም ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶቸ ሁሉ ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር(10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ስንዱ ወስጥ በተገለፀው አድራሻ በአካል በመገኘት የመኪኖቹን ይዞታ መመልከት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሽከርካሪ የመነሻ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የማይመለስ ብር 500 (ብር አምስት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር 7ኛ ፎቅ በሚገኘው የሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ጨረታው መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ በ9፡00 ታሽጎ በቀጣዩ ቀን መስከረም 09 ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች ስለጨረታ ሰነዱ አሞላል እንዲሁም ሌሎች ከጨረታው ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠውን ዝርዝር በመከተል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ከነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጅምሮ እስከ መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ በ9፡00 ሰአት ድረስ ብቻ ከታች በተቀመጠው የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት የመጫረቻ ስነዶቻቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከተጠቀሰው ሰአት ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  7. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ

አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ሊሴ ገ/ማርያም ት/ቤት ጀርባ

ጌትአስ ኢንተርናሽናል ህንፃ፡ 7ኛ ፎቅ

ኢሜል፡ melakug@habeshacement.com / hanaa@habeshacement.com

አዲስ አበባ

Save Tender